Connect with us
Express news


Football

በቻምፒዮንስ ሊጉ በአስደናቂ ሁኔታ ከኋላ ተነስተው ያሸነፉ ቡድኖች! – ክፍል 3

Greatest Champions League Comebacks Ever! – Part III
fcbarcelona.com

በቻምፒዮንስ ሊጉ በአስደናቂ ሁኔታ ከኋላ ተነስተው ያሸነፉ ቡድኖች ላይ የጀመርነውን ተከታትይ ትንተና  የምንግዜም እጅግ አስደናቂ የሆኑትን አራት በመመልከት ይጠናቀቃል!

4. ሮማ 3 – 0 ባርሴሎና – (በድምሩ 4-4 ፣ ሮማ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ጎል አሸንፏል) ፣ 2018

youtube.com

በዚህ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሜዳው 4-1 ተሸንፎ እንደመምጣቱ የሮማው አለቃ ዩሴቢዮ ዲ ፍራንቼስኮ ለተጫዋቾቹ አንድ ምክር ሰጥቷል ፣ ግብ እንዳይቆጠርባችሁ። ለሮማ ከሜዳው ውጪ የጎል ስጦታ የሰጠው ዜኮ ነበር ፣ በድጋሚም መመሪነቱን የሰጣቸው እሱ ነበር። አሁን ጨዋታው ክፍት ነበር።

ዳንየል ዴ ሮሲ የፍፁም ቅጣት ምቱን አስቆጥሮ ሮማን የሁለት ግብ መሪነት ከሰጠ በኋላ ባርሴሎና በሊዮኔል ሜሲ እና በሉዊስ ሱዋሬዝ ጥሩ ሙከራ አድርጓል። ነገር ግን ሰአቱ ሄደ እና ሮማም ቀጠለ ፣ በ82ኛው ደቂቃ ላይ ስታዲዮ ኦሊምፒኮ ኮስታስ ማኖላስ በግንባሩ ያስቆጠረውን ጎል ተከትሎ በጩኸት ተናውጧል።

3. ሪያል ማድሪድ 1-4 አያክስ (በድምሩ 3-5)፣ 2019

youtube.com

የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ በአምስተርዳም አያክስን 2-1 ሲያሸንፍ በአውሮፓ እግር ኳስ ላይ ያለው የስልጣን ዘመን እራሱን የበለጠ የሚያራዝም መስሎ መታየት ጀመረ ያም ብዙ የሚያስደንቅ አልነበረም።

ሪያል በበርናባው ሁለት ጊዜ ግብ ይቆጠርበታል የሚለው ሀሳብ ፈጽሞ የማይቻል መስሎ ነበር ነገር ግን በዚህ ፍርሃት የለሽ ወጣት የአያክስ ቡድን በግሩም ሁኔታ ተበልጧል። ጎብኝዎቹ ባሳዩት አስደናቂ እንቅስቃሴ በአንድ ሰአት ውስ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር በወቅቱ የአውሮፓ ሻምፒዮኖችን ተስፋ በእጅጉ መናድ ችለዋል።

70ኛው ደቂቃ ላይ ማርኮ አሴንሲዮ ያገባው ኳስ በባለሜዳዎቹ በኩል አጭር መነቃቃትን ፈጥሯል ፣ ነገር ግን ከሁለት ደቂቃ በኋላ በላሴ ሾን ግሩም የሆነ ቅጣት ምት ግብ ጨዋታው ተገድሏል።

በአራት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሪያል ማድሪድ ከዩሲኤል ተሸንፎ ወደቀ!

2. ኤሲ ሚላን 3-3 ሊቨርፑል (ሊቨርፑል በፍፁም ቅጣት ምት 3-2 አሸንፏል)፣ 2005

youtube.com

የእንግሊዝ እና የአዉሮፓ እግር ኳስን ከተቆጣጠረ ረዥም ጊዜ የሆነው ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ለማሸነፍ ከፍተኛ ተጠባቂ የነበረው የካርሎ አንቸሎቲ ኤ.ሲ.ሚላን ፊት ለፊት ገጥሞታል።

በመጀመርያው አጋማሽ ጣሊያኖቹ ምርጥ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር ፣ እናም ቀያዮቹ እስከ እረፍት 3-0 በሆነ ውጤት በመመራታቸው እድለኛ ነበሩ በርካታ የሊቨርፑል ደጋፊዎችም ስታዲየሙን ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል።

ሆኖም የሊቨርፑሉ አምበል ስቴቨን ጄራርድ በሚወደው ክለቡ ተስፋ አልቆረጠም። አንጋፋው አማካይ ሊቨርፑልን በ53 ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ጎል አስቆጥሮ ተስፋ የሰጠ ሲሆን ከአንድ ደቂቃ በኋላ ቭላድሚር ሽሚከር ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል። ከዛም ዣቢ አሎንሶ ከፍፁም ቅጣት ምት የተተፋ ኳስ አግኝቶ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታውን አቻ አድርጓል።

ተጨማሪ ሰአት ሚላን ተቆጣጥሮ ነበር ነገርግን የሊቨርፑል አዲስ መንፈስ ሊሰበር አልቻለም። በፍፁም ቅጣት ምት ጣሊያኖቹ መጥፎ የነበሩ ሲሆን ይህም ዋንጫውን ለቀያዮቹ አሳልፎ ሰጥቷል። የጄርዚ ዱዴክ የግብ ጠባቂ ብቃት የአንድሪይ ሼቭቼንኮን ፍፁም ቅጣት ምት በሚያስደንቅ ሁኔታ አድኖ ለእንግሊዙ ቡድን አሸናፊነቱን ሰጥቷል.

1. ባርሴሎና 6-1 ፓሪስ ሴንት ጀርሜን (በድምሩ 6-5)፣ 2017

በ2017 ፒኤስጂ ባርሴሎናን 4-0 በሆነ የመጀመሪያ ጨዋታ ሲያሸንፍ ብዙዎች ይህ ተምሳሌታዊ ለውጥ ነው ብለው አስበው ነበር – የታሪካዊው እና ሃያሉ የባርሴሎና ቡድን መገልበጥ ፣ ለእግር ኳስ አዲሱ ሀያል ፒኤስጂ ጥሩ ድል ነበር።

ሆኖም በሁለተኛው ጨዋታ ሉዊስ ሱዋሬዝ ከሶስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ጎል ካስቆጠረበት ጊዜ አንስቶ ተመልሶ አሸንፎ ማለፉ የሚቻል ይመስል ነበር። በራስ ላይ ከተቆጠረ ጎል እና ከሊዮኔል ሜሲ ፍፁም ቅጣት ምት በኋላ ስፔናውያኑ አንድ ግብ ብቻ ነበር የሚያስፈልጋቸው። ሆኖም በ62 ኛው ደቂቃ የፒኤስጂው ኤድሰን ካቫኒ ያስቆጠረው ድንቅ ግብ በትረካው ውስጥ ያልተጠበቀ ነገር ነበር። ባለሜዳዎቹ አሁን ከ30 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውሰጥ ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር እና ምንም ጎል ሊቆጠርባቸውም አይገባም ነበር።

ሰዓቱ 87 ኛ ደቂቃ ላይ ሲደርስ ፣ በመጨረሻዎቹ ስምንት ውስጥ የፒኤስጂ ቦታ የተረጋገጠ ይመስል ነበር ፣ ነገር ግን በስምንት ደቂቃዎች የባርሴሎና ምርጥ እንቅስቃሴ ተሰረቀ። የኔይማር ቅጣት ምት እና የፍፁም ቅጣት ምት ግቦች በካምፕ ኑ የተስፋ ስሜት ፈጠሩ ፣ በ95 ደቂቃ በሰርጊ ሮቤርቶ ቮሊ ግብ በድምሩ 6-5 አሸንፈው ወደ ሩብ ፍፃሜው ሲያልፉ ስታዲየሙ ተናወጠ!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football