Connect with us
Express news


Football

በወሳኝ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ጣሊያን እና ስዊዘርላንድ ይፋለማሉ!

Italy and Switzerland Face-Off in Crucial World Cup qualifying Clash!
dailysportsng.com

የምድብ ሶስት ሁለቱ ምርጥ ቡድኖች ጣሊያኖች እና ስዊዘርላንዶች ፣ ወሳኝ በሆነ የ2022 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ፍልሚያ ላይ ይገናኛሉ።

ሁለቱም ቡድኖች ቢያንስ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ፣ ነገር ግን ሁለቱ ቡድኖች ካደረጓቸው 6 ግጥሚያዎች እኩል 14 ነጥቦችን በመሰብሰብ አንደኛ ደረጃን ለመያዝ ይፋለማሉ።

የሮቤርቶ ማንቺኒ ጣሊያን በዚህ ምድብ ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች አራቱን ግጥሚያዎች አሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል። በነዚህ ጨዋታዎች 12 ግብ አስቆጥረው አንድ ጊዜ ብቻ የተቆጠረባቸው ሲሆን ይህም ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት የምድቡ መሪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ነገር ግን አርብ በሮም ተመሳሳይ ነጥብ ከሰበሰበው ስዊዘርላንድ ጋር ይፋለማሉ።

ሎሬንዞ ፔሌግሪኒ እና ኒኮሎ ዛኒዮሎ በጉዳት ምክንያት ከጣሊያን ቡድን ለመውጣት የተገደዱ ሲሆን ማርኮ ቬራቲ እና ሲሮ ኢሞብሌ ባለፉት ሁለት የማጣሪያ ጨዋታዎች አልተካተቱም ነበር።

ፌዴሪኮ በርናርዲስቺ በመሀል ሜዳ ለአስተናጋጆቹ የሚሰለፍ ይመስላል ፣ ሎሬንዞ ኢንሲኔ እና ፌዴሪኮ ቺሳ ደግሞ በአጥቂው ስፍራ ላይ የሚሰለፉ ይሆናል።

independent.co.uk

ጆርጊንሆ እና ኒኮ ባሬላ በመሃል መስመር ላይ ከማኑዌል ሎካቴሊ ጋር ሊጣመሩ ይችላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጆርጂዮ ቺሊኒ ከቤልጂየም ጋር ባድደረጉት የመጨረሻ ጨዋታቸው ላይ የተላለፈበትን ቅጣት ካጠናቀቀ በኋላ በተከላካይ መስመሩ ከሊዮናርዶ ቦኑቺ ጋር የሚሰለፍ ይሆናል።

በስዊዘርላንድ በኩል ኒኮ ኤልቬዲ፣ ስቲቨን ዙበር፣ ብሬል ኤምቦሎ፣ ግሬጎር ኮበል እና ክርስቲያን ፋሲናች በጉዳት የማይገኙ ሲሆኑ ግራኒት ዣካ እና ሃሪስ ሴፌሮቪች ለሙራት ያኪን ቡድን አይሰለፉም።

ዴኒስ ዘካሪያ ቅጣቱን ካጠናቀቀ በኋላ ተመልሶ የሚገባ ይሆናል ፣ እና የ 24 አመቱ ወጣት በአማካይ ክፍል ውስጥ ለጎብኚዎቹ በጊዜ ተመልሶ በግጥሚያው ይሰለፋል።

tbrfootball.com

ማሪዮ ጋቭራኖቪች ለሀገሩ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች 16 ጊዜ ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በዚህ ግጥሚያ ላይ በምርት 11 የሚካተት ይሆናል እናም ሬናቶ ስቴፈን እና ሼርዳን ሻኪሪም የፊት መስመር ላይ ሊሰለፉ ይችላሉ።

ስዊዘርላንድ አርብ ላይ ከዚህ ግጥሚያ አንድ ነገር ይዘው ለመውጣት የሚያስችል አቅም አላቸው ፣ ነገር ግን ጎብኚዎቹ አንዳንድ ቁልፍ ተጫዋቾችን አጥተዋል ። ይህ በሁለት ጠንካራ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ከፍተኛ ፉክክር የርሚታይበት እና በተቀራራቢ ውጤት የሚጠናቀቅ ግጥሚያ እንጠብቃለን። ነገር ግን ጣሊያን በሜዳቸው ሶስቱን ነጥቦች ይወስዳሉ። ጣሊያን 1-0 በሆነ ውጤት ያሸንፋል ብለን እንገምታለን።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football