Connect with us
Express news


Football

ኡራጓዮች በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነጥቦች ከአርጀንቲናዎች መውሰድ ይችላሉ?

Can Uruguay Steal the Much-Needed Points from Argentina?
cadenapolitica.com

ኡራጓዮች ከአንድ ወር በፊት በቦነስ አይረስ አሳዛኝ ሽንፈት ካስተናገዱ በኋላ አሁን በሜዳቸው አርጀንቲናዎችን ለመበቀል ተስፋ አድርጓል።

አርጀንቲናዎች በደቡብ አሜሪካ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ከብራዚሎች በመቀጠል በ25 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። እስካሁንም ብራዚል እና አርጀንቲና በምድቡ አንድም ሽንፈት ያላስተናገዱ ሁለት ቡድኖች ናቸው።

በአንፃሩ ኡራጓዮች በ16 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ይህ ማለት እዚያ የሚቆዩ ከሆነ ወዲያውኑ ብቁ አይሆኑም ፣ የግድ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ውስጥ ማለፍ አለባቸው። ቺሊዎች በ13 ነጥብ ኡራጋዮችን በቅርበት በመከታተል ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ እናም ላ ሰለስቴዎች ነገ ምሽት ቢያንስ አንድ ነጥብ ለማግኘት የተቻላትን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሁለቱ አሳፋሪ ሽንፈቶች ፣ መጀመሪያ በአርጀንቲና 3-0 ከዛ በብራዚል 4-1 ፣ ካስተናገዱ በኋላ የኡራጓይ ደጋፊዎች ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል ፣ እናም አሰልጣኙ ኦስካር ታባሬዝ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ይገኛል።

ኡራጓዮች ባደረጓቸው የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት ያስተናፈዱ ሲሆን አርጀንቲናዎች ግን እስካሁን አንድም ሽንፈት አልቀመሱም። እንዲሁም ከሃምሌ 2019 ጀምሮ አንድም ሽንፈት አላስተናገዱም ፣ ይህ ማለት 25 ተከታታይ ግጥሚያዎች ማለት ነው! ሌሎች ውጤቶች በእነሱ መንገድ የሚሄዱ ከሆነ በዚህ ወር ውስጥ የዓለም ዋንጫ ቦታቸውን ሊያረጋግጡ ይችላሉ።

በሚያሳዝን ሁኔታ በጉዳት ላይ የሚገኘው የማንቸስተር ዩናይትድ ኮከብ አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ ለኡራጓዮች አይሰለፍም። ስለዚህ ሉዊስ ሱዋሬዝ ከ ታዳጊው ፋኩንዶ ቶሬስ ጋር ሆኖ የአጥቂ ክፍል ሙሉ ኋላፊነቱ ይወስዳል።

https://www.sport.es/

ሊዮኔል ሜሲ መጫወት ይችል እንደሆነ አሁንም ግልፅ አይደለም። የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጫዋች በጉልበት ችግር ምክንያት ለብድኑ መሰለፍ አልቻለም ነበር ፣ ነገር ግን አሁንም በአርጀንቲና ቡድን ውስጥ ተካቷል። መጫወት ካልቻለ አርጀንቲናዎች ሰፋ ያለ የተጫዋቾች አማራጭ አላቸው እናም ተተኪ ማግኘቱ ቀላል ይሆናል ፣ ፓውሎ ዲባላም ለግጥሚያው የመምረጥ እድሉ ሰፊ ነው።

ሁሉም ነገር ግምት ውስጥ ስናስገባ ኡራጓዮች ፣ በራስ የመተማመን ስሜት ካላቸው አርጀንቲናዎች ነጥብ መውሰድ የሚያስችላቸው አቅም አላቸው ብለን አናስብም እና ኡራጓዮች ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈት ያስተናግዳሉ ብለን እንጠብቃለን ፣ በተለይ ደግሞ ሜሲ ወደ ሜዳ ከተመለሰ እና አንዳንድ አስማታዊ ብቃቱ ማሳየት ከቻለ።  

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football