ወደ አለም ዋንጫው እነማን አለፉ ፣ እነማን አሁንም እየታገሉ ነው እና በሚቀጥለው አመት በኳታር ከሚደረገው ውድድር ውጪ የሆኑት እነማን ናቸው? ሁሉም ክስተቶች እና አነጋጋሪ ነጥቦች እነሆ!
ምድብ አራት
ፈረንሳይ 8 – 0 ካዛክስታን
የአለም ሻምፒዮን ፈረንሳይ ካዛኪስታንን 8 ለ 0 በማሸነፍ በቀጣዩ አመት በኳታር በሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ መቀላቀሉን ሲያረጋግጥ ፣ ክሊያን ምባፔ ከ1985 በኋላ የውድድር ሀትሪክ መስራት የቻለ የመጀመርያው የፈረንሳይ ተጫዋች ሆኗል።
ካዛክስታን አሁን እንደገና ተጠናክረው ማክሰኞ ከተቀናቃኛቸው ታጂኪስታን ጋር ለሚያደርጉትን አለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ መመልከት አለባቸው።
Bosnia-Herzegovina 1 – 3 Finland
ፊንላንዳውያን በቦስኒያ ሄርዞጎቪና ወደሚገኘው ዜኒካ ተጉዘው ከሜዳቸው ውጪ ፤ በማርከስ ፎርስ ፣ በዳንኤል ኦ ሻግኒሲ እና በሮቢን ሎድ ግቦች 3-1 አሸንፈዋል።
ፊንላንድ አሁን በምድብ አራት 11 ነጥብ በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ እናም ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር የመግባት ጥሩ እድል ያላቸው ይመስላል። ቦስኒያ-ሄርዞጎቪናዎች በ7 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆነዋል።
ምድብ አምስት
ቤልጂየም 3 – 1 ኢስቶኒያ
የዓለም ቁጥር አንድ ቤልጂየሞች ኢስቶኒያዎችን በማሸነፍ በኳታር ለሚደረገው የ2022 የዓለም ዋንጫ ውድድር አልፈዋል። ክርስቲያን ቤንቴኬ ፣ ያኒክ ካራስኮ እና ቶርጋን ሃዛርድ ለአስተናጋጁ ጎል አስቆጥረዋል። ኤሪክ ሶርጋ ለእንግዶቹ የማጽናኛ ጎል አስቆጥሯል።
insidesport.in
ኢስቶኒያዎች ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ቢሆኑም ማክሰኞ ቼክ ሪፐብሊኮችን መግጠም አለባቸው።
ዌልስ 5 – 1 ቤላሩስ
ጋሬዝ ቤል ለዌልሶች 100ኛ ጨዋታውን ባደረገበት ግጥሚያ ላይ ቤላሩሶችን በአስደናቂ ሁኔታ በማሸነፍ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ አምስት 2ኛ ደረጃን አግኝተዋል።
walesonline.co.uk
ዌልሶች ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ኢስቶኒያዎችን የግብ ማሸነፍ ካለባቸው እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡ ቼክ ሪፐብሊኮች በሦስት ነጥብ ከፍ ብለው ተቀምጠዋል። ቤላሩሶች ለአለም ዋንጫው ብቁ መሆን አልቻሉም። በቀጣይም በወዳጅነት ጨዋታ በአማን በሚገኘው ኪንግ አብዱላህ ስታዲየም ጆርዳኖችን ይገጥማሉ።
ምድብ ሰባት
ኖርዌይ 0 – 0 ላቲቪያ
ኖርዌይ እና ላቲቪያ በኦስሎ በሚገኘው ኡሌቫአል ስታዲዮን 0-0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
ኖርዌያኖች አሁንም በ2022 የአለም ዋንጫ ለመሳተፍ እየጣሩ ናቸው። በምድብ ሰባት በ18 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ፣ ነገር ግን ከመሪዎቹ ኔዘርላንዶች በ2 ብቻ የራቁ ሲሆን ማክሰኞ ደግሞ እርስ በእርስ የሚገናኙ ይሆናል። ላትቪያዎች በቀጣይ ጨዋታቸው ጂብራልተሮችን ይገጥማሉ።
ኔዘርላንድ 2 – 2 ሞንቴኔግሮ
ሞንቴኔግሮዎች በአለም ዋንጫ ማጣርያ ከ ኔዘርላንዶች ጋር ባደረጉት ግጥሚያ ላይ በመጨረሻዎቹ 10 ደቂቃዎች ሁለት ግቦችን አስቆጥረው አቻ የተለያዩ ሲሆን የምድብ ሰባት የደረጃ ሰንጠረዥን ሚዛናዊ ማድረግ ችለዋል። የሜምፊስ ዴፓይ ሁለት ግቦች በኢሊያ ቩኮቲክች እና ኒኮላ ቩጅኖቪች ጎቦች ተሰርዘዋል።
besoccer.com
ሆላንዳውያን የምድቡ መሪ ሆነው ቢቀጥሉም ቱርክ እና ኖርዌይ ግን በሁለት ነጥብ ብቻ ርቀው በቅርብ ርቀት እየተከታተሏቸው ነው።
ቱርክ 6 – 0 ጂብራልተር
ቱርኮች ጂብራልተሮች ላይ 6 ግብ አስቆጥረው የአለም ዋንጫ ህልማቸውን በህይወት ለማቆየት ችለዋል። ሙሀመድ ከረም አክቱርኮግሉ ፣ ሜሪህ ዴሚራል፣ ሰርዳር ዱርሱን እና ሜርት ሙልዱር ሁሉንም አንድ ግብ ሲያስቆጥሩ ሃሊል ዴርቪሾግሉ ሁለት ግብ አስቆጥሯል።
ጂብራልተሮች በ0 ነጥብ መጨረሻ ላይ ተቀምጠዋል። ቱርኮች አሁን በምድብ ሰባት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ናቸው። በሚቀጥለው ሳምንት ሞንቴኔግሮዎችን የሚገጥሙ ሲሆን በመሪዎቹ ኔዘርላንዶች ላይ ጫና ለመፍጠር የግድ 3ቱን ነጥብ ያስፈልጋቸዋል።