Connect with us
Express news


Football

አርጀንቲናዎች በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ብራዚሎችን ይገጥማሉ!

Argentina Battle Brazil in Mammoth World Cup Qualifier!

በደቡብ አሜሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያ ውስጥ ሁለት ምርጥ ቡድኖች የሚያደርጉት ፍልሚያ! አርጀንቲናዎች ወደ አለም ዋንጫው በማለፍ በኳታር ከብራዚሎች ጋር መቀላቀል ይችላሉ?

ማክሰኞ ምሽት ላይ በ2022 የአለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አርጀንቲናዎች መሪዎቹን ብራዚሎችን በሳን ሁዋን ፣ ስታዲዮ ሳን ሁዋን ዴል ቢሴንቴናሪዮ ስታዲየም ያስተናግዳሉ።

የሊዮኔል ስካሎኒ አርጀንቲና ባለፈው ጊዜ ኡራጓይን 1-0 በሆነ ውጤት ያሸነፉ ሲሆን ፣ ከኮሎምቢያዎች ጋር የተደረገው የሴሌካኦ ግጥሚያም በተመሳሳይ ውጤውት የተጠናቀቀ ሲሆን ይህም ብራዚሎች ወደ 2022 የኳታር የአለም ዋንጫ ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ኡራጓይን ባሸነፉበት ግጥሚያ ላይ ከተጠባባቂ ወንበር ላይ በመጨረሻው ሩብ ሰአት ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን ፣ ስካሎኒ ተጫዋቹ ከብራዚል ጋር ለሚኖረን ግጥሚያ እንዲዘጋጅ ያግዘዋል ብሏል።

news.cgtn.com

ሜሲ አሁን በምርጥ 11 ሊካተት ይችላል ይህ ማለት ላውታሮ ማርቲኔዝ ወይም ፓውሎ ዲባላ በጨዋታው ላይካተቱ ይችላሉ ማለት ነው።

ስካሎኒ ኡራጓይን ባሸነፈበት ግጥሚያ ላይ ይዞት የገባው አሰላለፍን ምንም አይነት ለውጥ ማድረግ አያስፈልገውም ፣ክርስቲያን ሮሜሮ እና ኒኮላስ ኦታሜንዲ ከኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ጋር በግብ ክልል አካባቢ በድጋሚ ይዞ የሚገባ ይሆናል።

ብራዚልን በተመለከተ ዋና አሰልጣኝ ቲቴ ያለ ካሴሚሮ የሚጫወቱ ሲሆን ፣ ኤደንልሰን በእሱ ቦታ ለመጫወት ተጠርቷል።

playcrazygame.com

ይሁን እንጂ ፋቢንሆ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ከግጢያው ለመራቅ በመገደዱ ፣ በእሱ ምትክ የመሰለፍ እድል እንደሚሰጠው ተስፋ አድርጓል ፣ ነገር ግን የፍሬድ ቦታ ከኮሎምቢያ ጋር በነበራቸው ግጥሚያ ላይ በግማሽ ሰዓት ተቀይሮ ከወጣ በኋላ በምርጥ 11 የመካቅተቱ ጉዳይ አደጋ ላይ ወድቋል።

ምንም እንኳን ቪኒሲየስ ጁኒየር በአጥቂ ክፍሉ ለመካተት ተስፋ ቢያደርግ እና ማለፋቸውን ቢረጋገጥም ፣ ቲት ለእንደዚህ አይነቱ ትልቅ ግጥሚያ ብዙ ለውጦችን ያደርጋል ብለን አንጠብቅም።

ጨዋታው በሁለቱም አጋማሽ በተገኙ አንዳንድ ግቦች 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብለን እናስባለን።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football