Connect with us
Express news


Football

ቶተንሃም በእሁድ ፍጥጫ ሊድስን ያስተናግዳል!

Tottenham to Entertain Leeds in Sensational Sunday Showdown!
cartilagefreecaptain.sbnation.com

አንቶኒዮ ኮንቴ አሁንም ለስፐርስ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ድሉን እየጠበቀ ነው። ሊድስ ከወራጅ ቀጠናው ርቆ ለመውጣት ይፈልጋል። ሁለቱ ቡድኖች በእንግሊዝ ዋና ከተማ ሲገናኙ ምን ይሆናል?

ቶተንሃም ሆትስፐር በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) በሰሜን ለንደን ከሊድስ ዩናይትድ ጋር እሁድ ሲጫወት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኘት ይፈልጋል።

በአንቶኒዮ ኮንቴ የመጀመርያ የሊግ ጨዋታ ከኢንተርናሽናል ዕረፍት በፊት ስፐርሶች ከኤቨርተን ጋር 0-0 በሆነ ውጤት ሲለያዩ ሊድስም ከሌስተር ሲቲ ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተው አንድ ነጥብ አግኝተዋል።

ወደዚህ ግጥሚያ ሲገቡ አስተናጋጆቹ እስካሁን ካደረጓቸው 11 ጨዋታዎች በ16 ነጥብ በኢፒኤል 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ተጋጣሚያዎቻቸው በ11 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ክርስቲያን ሮሜሮ በኢንተርናሽናል እረፍት ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ቶተንሃሞች እሁድ ያለ እሱ መግባት ይኖርባቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጆቫኒ ሎ ሴልሶ ከአርጀንቲና ግዳጅ ከጉዳት ጋር ተመልሷል እና ለኮንቴ መሰለፉ እርግጠኛ አይደለም።

አማካዩ ኦሊቨር ስኪፕ በቅጣት ምክንያት የማይሰለፍ ቢሆንም ሪያን ሴሴኞን እና ብራያን ጊል ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ልምምድ ተመልሰዋል።

ሃሪ ዊንክስ ፣ ታንጉይ ንዶምቤሌ በሜዳው መሀል ላይ ከፒየር-ኤሚል ሆጅብጀርግ ጋር እንዲሰለፍ ለማድረግ ቦታውን መልቀቅ ሊኖርበት ይችላል ፣ በኋላ 3 መስመር ላይ ያለው የሮሜሮ ቦታም በዳቪንሰን ሳንቼዝ ሊወሰድ ይችላል።

goal.com

ሃሪ ኬንም ከፊት መጀመር አለበት እና እንግሊዛዊው ኮከብ በውድድር አመቱ ያስቆጠረው አንድ ብቸኛ የኢ.ፒ.ኤል ጎል ላይ ለመጨመር ይፈልጋል።

በሊድስ በኩል ፓትሪክ ባምፎርድ እና ሉክ አይሊንግ በጉዳት ከሜዳ እንደሚርቁ ሲገለፅ ሮቢን ኮች እንዲሁ ለማርሴሎ ቢኤልሳ ቡድን በዚህ ጨዋታ አይሰለፍም።

ጄሚ ሻክልተን እና ጁኒየር ፊርፖ ሁለቱም ሊሳተፉ ይችላሉ ፣ ግን የኋለኛው በምርጥ 11 ውስጥ በግራ ተከላካይ ቦታ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል ፣ ፓስካል ስትሩይክ ወደ ተቀያሪ ወንበር እንደሚወርድ ይጠበቃል።

ዳንኤል ጀምስ ባምፎርድ ሲለሌለ ወደ መሀል አጥቂ ቦታ ሊገባ የሚችል ሲሆን ጃክ ሃሪሰን ፣ ሮድሪጎ እና ራፊንሃም በፊት መስመሩ ላይ ይገኛሉ።

skysports.com

ሊድስ ይህንን ለኮንቴ የማይመች ጨዋታ ለማድረግ አቅሙ አላቸው። ሆኖም ስፐርስ ጠባብ ድል እንደሚያስመዘግብ እየጠበቅን ነው። የኛ ግምት በሰሜን ለንደን የሚደረገው ጨዋታ 1-0 እንደሚጠናቀቅ ሲሆን ግቡም በሁለተኛው አጋማሽ ይቆጠራል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football