Connect with us
Express news


Football

ቼልሲ በቻምፒየንስ ሊግ አራት ግብ አስቆጥሮ ጁቬንቱስን አሸነፈ!

Amazing Chelsea Fire Four Past Juventus in Champions League!
standard.co.uk

ሰማያዊዎቹ ጁቬንቱስን በለንደን በቀላሉ ባሸነፉበት ግጥሚያ ላይ ፤ ቻሎባ ፣ ጀምስ ፣ ሁድሰን-ኦዶይ እና ቨርነር ግብ አስቆጥረዋል።

ቼልሲዎች ትሬቮህ ቻሎባህ፣ ሬስ ጀምስ፣ ካልም ሁድሰን-ኦዶይ እና ቲሞ ወርነር ግብ አስቆጥረው ጁቬንቱስን 4-0 አሸንፈዋል። ሰማያዊዎቹ በአሁን ሰአት በቻምፒየንስ ሊግ ምድብ ስንትን እየመሩ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።

የቶማስ ቱቸል የአውሮፓ ሻምፒዮናዎች ከመጀመሪያው ጀምሮ ግጥሚያዉን ተቆጣጥረው ነበር እና በምርጥ 16 ውስጥ ቦታቸውን አስመዝግበዋል ።

የ22 አመቱ ተከላካይ ቻሎባህ በ25ኛው ደቂቃ ላይ የመሀል ተከላካዩ አንቶኒዮ ሩዲገር ፣ ሃኪም ዚያች ያሻማዉን የመአዝን ምት በደረቱ ካቀበለው በኋላ በስዚኒ መረብ ላይ አስቆጥሯል።

thesun.co.uk

በ 55ኛው ደቂቃ ሪይስ ጀምስ በግራ በኩል ወደ መአዝኑ ጥግ በማስቆጠር አስደናቂ ቴክኒክ አሳይቷል። ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ሁድሰን-ኦዶይ ከሩበን ሎፍተስ-ቼክ የተሻረበትን ኳስ በግራ እግሩ አስቆጥሯል።

remonews.com

ጁቬንቱስ ቀድሞውንም ወደ ምድብ ድልድሉ ማለፍ ችሏል ነገር ግን ውጤቱ ከቼልሲ ጋር በእኩል 12 ነጥብ በምድቡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣቸዋል።

ወርነር በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ከዚዬች የተሻገረለትን ኳስ በአስደናቂ አጨራረስ የቼልሲዎች የማሳረግያ ግብ አስቆጥሯል።

ጣሊያኖቹ ባለፈው መስከረም ወር በጣሊያን በተካሄደው የመጀመርያ ዙር ጨዋታ ቼልሲዎች 1-0 አሸንፈው መካከለኛ አቋም አሳይተዋል ፣ ሰማያዊዎቹ ደግሞ ጥሩ እንቅስቃሴ በማሳየት 20 የግብ ሙከራ ሲያደርጉ ፣ አርሮጊቶቹ ደግሞ ስምንት ሙከራዎችን አስመዝግበዋል።

በ28ኛው ደቂቃ ላይ የቀድሞ የቼልሲ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ለማሲሚላኖ አሌግሪ ቡድን ጥሩ እድል አግኝቶ የቸልሲውን ግብ ጠባቂ ኤዶዋርድ ሜንዲ በአናቱ ላይ ኳሱን አሳልፎ ግብ ለማስቆጠር የተቃረበ ቢሆንም የ37 አመቱ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ በጥሩ ሁኔታ ኳሱን አድኖታል።

ሜንዲ በሁለተኛው አጋማሽ መገባደጃ ላይ ዌስተን ማክኬኒ የመታዉን ኳስ አድኗል።

ስዚኒ ፤ ሁድሰን-ኦዶይ ፣ ጄምስ እንዲሁም ቤን ቺልዌል እና ዚዬች ያደረጓቸውን ለግብ የሚሆኑ ሙከራዎችን በማዳን ጁቬንቱስን ከውርደት አትርፏል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football