Connect with us
Express news


Football

ማግፒዎች ከቆሰለው አርሰናል ነጥብ ለመውሰድ ይፈልጋሉ!

Magpies Seek to Steal the Points at  Wounded Arsenal!
shieldsgazette.com

አርሰናል ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በሊቨርፑል ካጋጠመው ከባድ ሽንፈት ለማገገም ይፈልጋል። ኒውካስል ደግሞ ከወራጅ ቀጠናው ሊያወጣው የሚችለውን ድል አጥብቆ ይፈልጋል።

በሁሉም ውድድሮች 10 ጨዋታዎችን አንድም ሽንፈት ሳያስተናግድ የቆየው አርሰናል ባሳለፍነው ሳምንት በአንፊልድ ተቋጭቷል። መድፈኞቹ በቅዳሜው የፕሪምየር ሊግ የምሳ ሰአት መርሃ ግብር ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ አቅደዋል።

የለንደኑ ክለብ ባለፈው ጨዋታ 4-0 በሆነ ውጤት በሊቨርፑል ሲሸነፍ ኤዲ ሃው በኒውካስል የአሰልጣኝነቱ ዘመን የጀመረው ከብሬንትፎርድ ጋር 3-3 በሆነ አቻ ውጤት በመለያየት ነበር።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ የሚኬል አርቴታ ቡድን እስካሁን ካደረጋቸው 12 ጨዋታዎች 20 ነጥብ በመሰብሰብ በኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዥ 5ኛ ላይ ተቀምጧል። ማግፒዎች ከ36 ነጥቦች 6 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ መጨረሻ ላይ ይገኛሉ።

አርሰናል ለዚህ ጨዋታ ምንም አይነት አዲስ የጉዳት ችግር የለበትም እና ስዊዘርላንዳዊው አማካኝ ግራንት ዣካ አመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከጉልበት ጉዳቱ ሊመለስ ይችላል ይህም ለባለሜዳው ቡድን ትልቅ መነሳሳት ሊፈጥር ይችላል።

ሲአድ ኮላሲናች ከከባድ የቁርጭምጭሚቱ ችግር ማገገሙን ቀጥሏል ነገርግን ምንም ይሁን ምን በተከላካይ መስመሩ ላይ ለውጥ ሊኖር ይገባል ፣ ፖርቱጋላዊው የግራ ተከላካይ ኑኖ ታቫሬስን በአንፊልድ ደካማ አቋም ካሳየ በኋላ በኪይራን ቲዬርኒ የሚተካ ይሆናል።

sports-nova.com

ከቲየርኒ ዳግም ወደ ምርጥ 11 አሰላለፍ መመለስ ውጪ ፣ በአይንስሊ ማይትላንድ-ናይልስ ጫና ቢያጋጥመውም አልበርት ሳምቢ ሎኮንጋ በመሀል ሜዳ ቦታውን የሚያስጠብቅ ሲሆን ፣ መድፈኞቹ በድጋሚ ተመሳሳይ አሰላለፍ ይዘው የሚገቡ ይሆናል።

ኒውካስልን በተመለከተ ፋቢያን ሻር ከብሬንትፎርድ ጋር በነበራቸው ግጥሚያ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ከሜዳ ርቋል ስለዚህ ሃዌ በሶስት ተከላካዮች የሚገባ ከሆነ የስዊድኑ ተጫዋች ኤሚል ክራፍት በምርጥ 11 ሊካተት ይችላል።

premierleague.com

ጆ ዊሎክ በፊት መስመር ቦታ የመሰለፍ ዕድል አጥቶ የቀየ ቢሆንም ከቀድሞ ክለቡ ጋር ለመፋለም ይፈልጋል። አይዛክ ሃይደንም በተመሳሳይ ሁኔታ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ማርቲን ዱብራቭካ በግብ ጠባቂነቱ ቦታ ላይ ሲሰለፍ ማየት የሚያስደንቅ አይሆንም።

ፖል ዱሜት ለእንግዳው ቡድን እንደማይሰለፍ ብቸኛ እርግጥ የሆነ ተጫዋች ነው ፣ እና ሃው በኮቪድ-19 መያዙ ከተረጋገጠ በኋላ ለዚህ ጨዋታ ወደ ዋና ከተማ እንዲሄድ ይፈቀድለት እንደሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

አጥቂው አለን ሴንት-ማክሲሚን በሚሰለፍበት ጊዜ ኒውካስል ሁል ጊዜ አደገኛ ይመስላል። ይሁን እንጂ አስከፊ የተከላካይ መስመር እንዳላቸው ሪከርዳቸው ይናገራል። አርሰናል 2-1 እንደሚያሸንፍ እንጠብቃለን።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football