Connect with us
Express news


Football

ፒኤስጂ ሴንት-ኢቲየንን ከኋላ ተነስቶ 3-1 አሸነፈ!

PSG Power Back to 3-1 Victory at Saint-Étienne!
reuters.com

ምንም እንኳን በአንድ ግብ ልዩነት ቢመሩም ፣ የ ፒኤስጂ ኮከቦች ተጫዋቾች ትንሹ ሴንት-ኢቲየንን በጣም በልጠው ተገኝተዋል። ነገር ግን ኔይማር በቁርጭምጭሚት ጉዳት ከሜዳ ወጥቷል ይህም ለፖቸቲኖ ጥሩ ዜና አደለም!

ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ከአንድ ጎል መእራት ተነስቶ በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ የተገደደውን ሴንት ኤቲየን በማሸነፍ በ14 የነጥብ ልዩነት የፈረንሳይ ሊግ 1ን እየመራ ይገኛል።

ኔይማር ቀደም ብሎ ያስቆጠረውን ጎል ከጨዋታ ውጪ ሆኖ ከተሰረዘ በኋላ ዴኒስ ቦዋንጋ ሴንት ኢቲየንን በ23ኛው ደቂቃ መሪ አድርጓል።

ቲሞቴ ኮሎዲዚይክዛክ በኪሊያን ምባፔ ላይ በሰራው ጥፋት ቀይ ካርድ የተመለከተ ሲሆን ማርኩዊንሆስ ከእረፍት በፊት በተገኘው ቅጣት ምት ውጤቱን አቻ አድርጓል።

ግጥሚያው ሊጠናቀቅ 11 ደቂቃ ሲቀረው አንጄል ዲማሪያ ሁለተኛ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ፣ ማርኩዊንሆስ ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ሽርፍራፊ ሰከንድ ላይ ሶስተኛውን ግብ አስቆጥሯል።

የቦዋንጋ የመክፈቻ ግብ መጀመሪያ ከጨዋታ ውጪ በሚል ከተለከለ በኋላ በቫር ግብ ሆኖ ፀድቋል ፣ የማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ፒኤስጂ በ2021 የሊግ 1 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ግብ ሲያስተናግድ ለ11ኛ ጊዜ ነው። ይህም ከ2012 በኋላ በአንድ አመት ከፍተኛው የመክፈቻ ግብ ያስተናገደበት አመት ነው።

አንጋፋው ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስ ከሪያል ማድሪድ ከተዘዋወረ በኋላ ለፒኤስጂ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገ ቢሆንም ብድኑ የመክፈቻውን ግብ ከማስተናገድ መታደግ አልቻለም።

ሦስቱንም የሌዝ ፓሪሲየንስ ግቦች አመቻችቶ ያቀበለው ሊዮኔል ሜሲ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ኔይማር የሞከረውን ጥረት ተከትሎ ቡድኑን መሪ የኢያደርግበት ትልቅ እድል አባክኗል።

ነገር ግን አርጀንቲናዊው ተጫዋች በውጪው እግሩ ድንቅ የሆነ ለግብ የሚሆን ኳስ ለ ዲማሪያ እና ደግሞ በተጨማሪ ለማርኩዊንሆስ ሌላ ለግብ የሚሆን ኳስ በማቀብል ቡድኑን ክሷል ፣ ፒኤስጂም ቅድሜ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኒስ በሜፅ 1-0 ከተሸነፈች በኋላ የሊጉ መሪነትን አጠናክሯል።

marca.com

ሆኖም ሁሉም ነገር ለፒኤስጂ መልካም ዜና አልነበረም። ኔይማር በ85ኛው ደቂቃ ላይ ከባድ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ከሜዳ ወጥቷል።

eurosport.com

የክላውድ ፑኤል ሴንት ኢቴይን አሁን በሊግ 1 የደረጃ ሠንጠረዥ በሜትዝ እና ክሌርሞን ፉት በግብ ክፍያ ተበልጦ ግርጌ ላይ  ይገኛል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football