Connect with us
Express news


Football

መዶሻዎች በአስደሳች የለንደን የኢ.ፒ.ኤል ፍልሚያ ቼልሲን ያስተናግዳሉ!

Hammers to Host Chelsea in Exciting all-London EPL Clash!
aktualnezpravodajstvi.cz

ቼልሲ ቅዳሜ ወደ ዌስትሃም ሲጓዝ ምዕራብ ለንደን እና ምስራቅ ለንደን ይፋለማሉ። በዚህ ከባድ የደርቢ ግጥሚያ ማን ይሰለፋል እና ምን ይከሰታል?

ቼልሲዎች ቅዳሜ አራተኛ ደረጃ ላይ ወደተቀመጠው ዌስትሃም ዩናይትድ ሲጓዙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሪነታቸውን ወደ አራት ነጥብ ለማሳደግ ይፈልጋሉ።

ሰማያዊዎቹ ረቡዕ ከሜዳቸው ውጪ ዋትፎርድን 2-1 ካሸነፉ በኋላ ወደዚህ የለንደን ደርቢ ያቀናሉ። በተመሳሳይ ምሽት ዌስትሃም ከብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን 1-1 ተለያይተዋል።

የመሀል ተከላካዩ አንጄሎ ኦጎቦና ከረጅም ጊዜ የጉልበት ችግር ማገገም ባለመቻሉ በግጥሚያው ለመዶሻዎቹ የማይሰለፍ ሲሆን ነገር ግን የምስራቅ ለንደኑ ክለብ አሮን ክረስዌል ለግጥሚያው እንደሚያገግም ተስፋ አድርገዋል።

የክሪስዌል መመለስ ቭላዲሚር ኩፋል በተጠባባቂ ወንበር እንዲቀመጥ ሊያደርገው ይችላል ነገር ግን ሌላ ቦታ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አይኖርም። ስለዚህ ፣ ፓብሎ ፎርናልስ ፣ ሰኢድ ቤንራህማ እና ጃሮድ ቦወን በአጥቂው መስመር ከሚካኤል አንቶኒዮ ጀርባ በድጋሚ ይሰለፋሉ።

inews.co.uk

ዴቪድ ሞይስ ከግጥሚያዉ ጠቀሜታ አንፃር የአሰላለፍ ለውጥ ያደርጋል ተብሎ ባይጠበቅም ፤ ማኑዌል ላንዚኒ፣ ኒኮላ ቭላሺች እና የኮንጎው የግራ መስመር ተከላካይ አርተር ማሱዋኩ አሰላለፉ ለመቀየር ከሚመረጡት መካከል ይጠቀሳሉ።

በሌላ በኩል ማቲዎ ኮቫቺች እና ቤን ቺልዌል በጨዋታው ቼልሲ የማይሰለፉ ሲሆኑ ትሬቮህ ቻሎባህ ከዋትፎርድ ጋር ባጋጠመው የጡንቻ ጉዳት ይህንን ግጥሚያ እንደሚያመልጠው ይጠበቃል።

ቶማስ ቱቸል ምናልባት እሮብ ከተሰለፈው ስብስብ ብዙ ለውጦችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ፣ በዚህ መሰረትም ጆርጊንሆ ፣ ቲያጎ ሲልቫ እና ሮሜሎ ሉካኩ በምርጥ 11 ሊካተቱ ይችላሉምስ ።

beinsports.com

ንጎሎ ካንቴ እና ሬስ ጀምስ የመሰለፋቸው ጉዳይ ለእንግዶቹ አጠራጣሪ ሆነው ቆይተዋል ፣ ስለዚህ ሩበን ሎፍተስ ቼክ በአማካይ ሊጫወት ይችላል ፣ ሴሳር አዝፒሊኬታ ደግሞ በቀኝ ክንፍ ተከላካይ ይሰለፋል።

ቼልሲ ግጥሚያዉን በጠባብ ውጤት እንደሚያሸንፍ እንጠብቃለን። ሰማያዊዎቹ የመጀመርያውን አጋማሽ አሸንፈው ግጥሚያው 2-1 ያሸንፋሉ ብለን እናስባለን።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football