Connect with us
Express news


Football

በሰሜን ለንደን ስፐርስ እና ሶን ቀላል የኢፒኤል ድል አግኝተዋል!

Spurs and Son Earn Easy EPL Victory in North London!
cbssports.com

በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም ሶን በሁለቱም ጎሎች እጁ በነበረበት ጨዋታ ፣ ስፓርስ እስካሁን በኮንቴ መሪነት ምርጡን ብቃታቸውን አሳይተዋል።

ቶተንሃም ሆትስፐር በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀሙስ ምሽት በሰሜን ለንደን ብሬንትፎርድን 2-0 በማሸነፍ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

10ኛው ደቂቃ ላይ ስፐርሶች የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠሩ ሲሆን ፣ ሶን ሄንግ ሚን በአደገኛው ያሻገረውን ኳስ የብሪትፎርዱን ሰርጊ ካኖስ አወጣለሁ ብሎ በራሱ ጎል ላይ አስቆጥሯል።

dailynationtoday.com

የብሬንትፎርዱ ግብ ጠባቂ አልቫሮ ፈርናንዴዝ በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ የቶተንሃሙ አጥቂ ሃሪ ኬን ከተከላካዮች ጀርባ ገብቶ ያገኘውን ኳስ በመመለስ ጥሩ ብቃት አሳይቷል።

በ65ኛው ደቂቃ ላይ ቶተንሃሞች በከፍተኛ ፍጥነት በመልሶ ማጥቃት መሪነታቸውን ወደ ሁለት ከፍ አድርገዋል። ሰርጂዮ ሩጊሎን ለደቡብ ኮሪያዊው ሶን እንዲያስቆጥር አድርጎ ያቀበለውን ኳስ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮታል።

thetimes.co.uk

በስሎቬኒያ ሚኖው ኤን ኤስ ሙራ አሳፋሪ የኢሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ሽንፈት ከደረሰበት ከሳምንት በኋላ እና ወደ በርንሌይ ተጉዞ በበረዶ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ጨዋታው ከተራዘመ ከአራት ቀናት በኋላ ስፐርስ እስካሁን በአንቶኒዮ ኮንቴ ስር ምርጡን 90 ደቂቃዎች ተጫውቷል።

“ከአደገኛ ቡድን ጋር ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ። የተጫዋቾቹን ቁርጠኝነት እና ጥሩ ስሜት ስላየሁ ደስተኛ ነኝ” ሲል ኮንቴ ተናግሯል።

“ጥሩ ምላሽ ነው (ከባለፈው ሳምንት በኋላ) በሽንፈት ውስጥ ብዙ ነገር ትማራለህ አሁን ግን እሁድ (ከኖርዊች ሲቲ ጋር) ስለሌላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማሰብ አለብን” ሲል የስፐርሱ አለቃ ተናግሯል።

በቶማስ ፍራንክ ቡድን ላይ የታየው ጥሩ ብቃት ብዙ ግቦችን ማምጣት ነበረበት እናም የኬን የኢ.ፒ.ኤል. የግብ ድርቅ ቢቀጥልም ለቶተንሃም ጥሩ ምሽት ነበር። እንግሊዛዊው አጥቂ በዘንድሮው የውድድር ዘመን አንድ ጎል ብቻ ያስቆጠረ ሲሆን በአጥቂ ባልደረባው ሶን እየተበለጠ ነው።

የኮንቴ ቡድን በ13 ጨዋታዎች 22 ነጥብ በማግኘት አሁን ከምርጥ አራቱ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ብሬንትፎርድ 14 የከፍተኛ ሊግ ግጥሚያዎችን አድርጎ በ16 ነጥብ 12ኛ ላይ ተቀምጧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football