Connect with us
Express news


Football

አትላንታ በአስደናቂ ጨዋታ የሴሪኤው መሪ ናፖሊን አሸንፏል።

Atalanta Knock Napoli off Serie A Summit with Dramatic Victory!
football-italia.net

በኔፕልስ ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም የተደረገ ጨዋታ አታላንታ አሸናፊ። ናፖሊ የሴሪያውን ከፍተኛ ደረጃ አጥቷል!

ናፖሊ በሜዳው በአታላንታ 3-2 በመሸነፍ መሪነቱን በማጣት ወደ ሶስተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል ፣ በምርጥ አራት ውስጥ ያለውን ልዩነትም ወደ አራት ነጥብ ወርዷል።

የሉቺያኖ ስፓሌቲ ቡድን ከአንድ ግብ መመራት ተነስተው በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ መሪ መሆን ችለዋል። ሆኖም የቤርጋሞ ጎብኝዎች የናፖሊ የውድድር አመቱ ሽንፈትን ወደ ሁለት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

ውጤቱም ከአራተኛው ሳምንት ጀምሮ የሴሪአን መሪነት ይዞ የነበረው ግሊ አዙሪ በ36 ነጥብ ከአዲሱ መሪ ኤሲ ሚላን በሁለት ነጥብ እንና ከኢንተር ሚላን በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በሶስተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አስገድዶታል ፣ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአራተኛ ደረጃ ከተቀመጠው የጂያን ፒዬሮ ጋስፔሪኒ አታላንታ በሁለት ነጥብ ብቻ በልጦ ይገኛል።

ሩስላን ማሊኖቭስኪ በግራ እግሩ አስቆጥሮ በሰባተኛው ደቂቃ እንግዳዉን ቡድን ከፊት አስቀምጧል። ፒዮትር ዚኤሊንስኪ በአስደናቂው የመጀመርያው አጋማሽ መገባደጃ ላይ የአቻነት ግብ አስቆጥሯል።

italy24news.com

ከእረፍት መልስ ድሬስ ሜርቴንስ በጥሩ አጨራረs ከመረብ በማሳረፍ ባለኤዳው ቡድን መሪ እንዲሆን አድርጓል ፣ ይህም ቤልጄማዊው አጥቂ በአራት የሴሪአ ጨዋታዎች 5ኛ ግቡ ነበር።

አታላንታ አስደናቂ ምላሽ ሰጠ። ሜሪህ ዴሚራል በ66ኛው ደቂቃ ላይ የአቻነት ግቡ ከማስቆጠሩ በፊት ፣ ዱቫን ዛፓታ የተሻማለትን ኳስ በጭንቅላቱ በመምታት አስደናቂ ሙከራ አድርጎ ነበር።

የስዊዘርላንዱ ተጫዋች ሬሞ ፍሪዩለር ከአምስት ደቂቃ በኋላ ጆሲፕ ኢሊቺች ያቀበለውን ኳስ እመርብ ላይ በማሳረፍ እንግዳው ቡድን አሸንፎ እንዲወጣ አድርጓል።

gdnonline.com

አንድሪያ ፔታኛ ከመጨረሻው ፊሽካ በፊት በሳጥኑ ውስጥ ጥሩ እድል አግኝቶ ነበር ነገር ግን የናፖሊው አጥቂ ዕድሉ በአግባቡ መጠቀም አልቻለም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football