Connect with us
Express news


Football

ቶተንሃም እሁድ በአስደናቂ የኢ.ፒ.ኤል. ፍልሚያ ካናሪዎችን አሸነፋ!

Tottenham Destroy Canaries in Sensational Sunday EPL Showdown!
vbetnews.com

ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ካናሪዎችን ባሸነፈበት ግጥሚያ ላይ ሞራ አስደናቂ ጎል አስቆጥሯል በተጨማሪም ሶን እና ሳንቼዝም ለቡድናቸው ግብ አስቆጥረዋል!

የፊት አጥቂው ሉካስ ሞራ አስደናቂ ግብ እሁድ እለት ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ኖርዊች ሲቲን 3-0 እንዲያሸንፍ ረድቷል።

ሞራ የኖርዊች አማካዩን ቢሊ ጊልሞርን በማታለል እና ከሶን ሄንግ ሚን ጋር አስደናቂ የሆነ የኳስ ቅብብል ተጫውቶ ከሳጥኑ ውጪ መትቶ በማስቆጠር ቡድኑ መሪ እንዲሆን አድርጓል።

thesun.co.uk

ድሉ ስፐርስን አንድ ቀሪ ጨዋታዎች እያለው በ14 ጨዋታዎች 25 ነጥብ በመሰብሰብ እና ከመሪው ቡድን በ10 ነጥብ ዝቅ ብሎ አምስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አስችሎታል ፣ አዲሱ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴም ተጽኖ መፍጠሩን ቀጥሏል።

ኖርዊች የኳስ ቁጥጥርን ተቆጣጥረው ነበር ነገርግን የኮንቴን ጥሩ የተከላካይ መስመር ማለፍ አልቻሉም ፣ ስፐርስ በመልሶ ማጥቃት ጥሩ ስራ ሰርቷል።

ሞራ በ10 ደቂቃ አስደናቂ የመክፈቻ ግብ ከማስቆጠሩ በፊት ፣ ፊት አጥቂ ቴሙ ፑኪ ኖርዊችን በሶስተኛ ደቂቃ መሪ ለማድረግ ተቃርቦ ነበር ነገር ግን ፊንላንዳዊው ተጨዋች ኳሱን በቀጥታ ወደ ስፐርሱ ግብ ጠባቂ ሁጎ ሎሪስ ልኮታል።

The Canካናሪዎቹ ከእረፍት መልስ ጫና ፈጥረው ነበር ግን ነገር አዳም ኢዳህ ፣ ፑኪ ያደረገውን ሙከራ ገጭቶ ከተመለሰ በኋላ ያገኘውን አስደናቂ የግብ እድል መጠቀም አልቻለም።

በሁለተኛው አጋማሽ ኮሎምቢያዊው ተከላካይ ዴቪንሰን ሳንቼዝ ከማዕዘን ምት ተሻምቶ ኳስ ወደ እግሩ የመጣዉን ኳስ ወደ ግብ በመቀየር የስፐርስን እሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጎታል።

ሶን ከተከላካዩ ቤን ዴቪስ የተቀበለዉን ኳስ ከመረግ ጋር በማገናኘት የማሳረግያውን ግብ አስመዝግቧል።

inf.news

“ጥሩ ስነ ልቦና ያለን ይመስለኛል። ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም ጠንክረን እንሰራን ነው እና አንቶኒዮ የሚሰጠንን በሜዳ ላይ ለመተግበር እየሞከርን ነው። የአጨዋወት ስልታችን በከፍተኛ ጥንካሬ አትቅቶ መጫወት ነው። በጣም ጥሩ እየሰራን ነው” በማለት ሞራ ተናግሯል።

ውጤቱ ዲን ስሚዝ ኖርዊችን ከተረከበ በኋላ የመጀመርያ ሽንፈቱ ሲሆን በኢ.ፒ.ኤል.የደረጃ ሰንጠረዥ በወራጅ ቀጠናው እንዲቆዩ አድርጓቸዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football