Connect with us
Express news


Football

ፖርቶ እና አትሌቲኮ የዩሲኤል እጣ ፈንታቸው ለመወሰን ይፋለማሉ!

Porto and Atlético Lock Horns to Decide UCL Destiny!
intothecalderon.com

ለቱም ክለቦች አሁንም ወደ ዩሲኤል የመጨረሻ 16 የማለፍ እድል አላቸው።  ማን ይሰለፋል እና ውጤቱ ምን አይነት ውጤት እንጠብቅ?

ፖርቶ እና አትሌቲኮ ማድሪድ በዩኢኤፍኤ ሻምፒዮንስ ሊግ (ዩሲኤል) ምድብ ሁለት ውስጥ አሁንም ሁለተኛ ሆነው ለመጨረስ እየተፎካከሩ ባለበት ወቅት ማክሰኞ ምሽት በኤስታዲዮ ዶ ድራጎኦ ይገናኛሉ።

ባለሜዳዎቹ በአሁኑ ሰአት ወደ ጥሎ ማለፍ ውድድር የሚያሻግራቸው ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ይገኛሉ ነገር ግን አትሌቲኮ እና ኤሲ ሚላን ከሴርዮ ኮንሴኦ ፖርቶ ቡድን በአንድ ነጥብ ዝቅ ብለው ይገኛሉ።

በቡድን ዜና አማካዩ ማቴዎስ ዩሪቤ በቢጫ ካርዶች መብዛት ምክንያት በዚህ ጨዋታ የማይሰለፍ ሲሆን ማርኮ ግሩጂች እና ሰርጆ ኦሊቬራ የሜዳው ሞተር ክፍል ውስጥ የሚሰለፉ ይሆናል።

ojogo.pt

ፔፔ አሁንም በጡንቻ ጉዳት አጠራጣሪ ነው ነገር ግን ለማክሰኞ ብቁ ለመሆን የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው ተብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢቫን ማርካኖ እና ጆአዎ ማሪዮ ከሜዳ ርቀው የሚቆዩ ይሆናል።

አጉስቲን ማርቼሲን ፣ ዲዮጎ ኮስታን ተክቶ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል ፣ ፔፔ ለግጥሚያው የማይደርስ ከሆነ ደግሞ ፋቢዮ ካርዶሶ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ተጫዋች ቻንስል ምቤምባ ጋር በተከላካይ መስመር የሚሰለፍ ይሆናል።

በአትሌቲኮ በኩል ተከላካዩ ፌሊፔ በጨዋታው በአራተኛው ዙር ከሊቨርፑል ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ቀይ ካርድ ካርድ በመመልከቱ ታግዷል እና ስቴፋን ሳቪች በማሎርካ በተሸነፍፉበት ግጥሚያ ላይ በ13 ደቂቃ ባጋጠመው ጉዳት ከሜዳ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

ሆሴ ጊሜኔዝ ከጡንቻ ችግር ጋር እየታገለ ነው። ስለዚህ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጂኦፍሪ ኮንዶግቢያ እና ማሪዮ ሄርሞሶ ለአትሌቲኮ የአደጋ ጊዜ የመሀል ተከላካይ ጥምረት ሊፈጥሩ ይችላሉ፣ ቶማስ ሌማር እንደገና ወደ መሀል ሜዳ ሲቀላቀል።

football-espana.net

ሉዊስ ሱዋሬዝ እና ጆዋ ፌሊክስ ሁለቱም በተጠባባቂ ወንበር ላይ የተቀመጡት ባለፈው ጊዜ ቢሆንም አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ በእርግጠኝነት በዚህ ሳምንት ሁለቱን ተጫዋቾች ለማሰለፍ ያስባል።

የዚህ ጨዋታ ግምታችን 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ሲሆን ይህም ሁለቱም ቡድኖች ወደ መጨረሻው 16 ለማለፍ አይረዳቸውም።

የፖርቶ ተጠባቂ አሰላለፍ፡
ማርቼሲን ፤ ማናፋ ፣ ምቤምፓ ፣ ፔፔ ፣ ሳኑሲ ፤ ኦታቪዮ ፣ ግሩጂች ፣ ኦሊቬራ ፣ ዲያዝ ፤ ታሬሚ ፣ ኢቫኒልሰን

የአትሌቲኮ ማድሪድ ተጠባቂ አሰላለፍ፡
ኦብላክ ፤ ሎሬንቴ ፣ ሄርሞሶ ፣ ኮንዶግቢያ ፣ ሎዲ ፤ ኮሬያ ፣ ኮኬ ፣ ደ ፖል ፣ ሌማር ፤ ግሪዝማን ፣ ሱአሬዝ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football