Connect with us
Express news


Football

ሪያል ማድሪድ በታላቅ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ ኢንተር ሚላንን አሸነፈ!

Real Win Champions League Battle of the Giants!
realmadrid.com

ሪያል ማድሪድ ኢንተር ሚላን ባሸነፈበት ግጥሚያ ላይ ክሩስ እና አሴንሲዮ ለአስተናጋጁ ቡድን ግብ አስገኝተዋል። ሁለቱም ክለቦች አሁን ወደ መጨረሻው 16 አልፈዋል!

የ13 ጊዜ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ በ10 ሰው ለመጨረስ የተገደደው እና በሁለተኛነት ወደ መጨረሻው 16 ያለፈው ኢንተር ሚላንን በሜዳው በማሸነፍ የቻምፒየንስ ሊግ ምድብ አራትን በበላይነት አጠናቋል።

ኢንተር በስፔን ድል አድርጎ ምድቡን ተጋጣሚውን በልጦ መጨረስ ይችል ነበር ነገር ግን የሴሪአው ቡድን ዕድሉን መጠቀም አልቻለም።

ላውታሮ ማርቲኔዝ ከቅርብ ርቀት የመታዉን ኳስ ፣ ኤዲን ዲዜኮ ወደ ግብ ጠባቂው ቲቦ ኮርቱዋ በቀጥታ በግንባሩ ገጭቶ የሞከረው ኳስ እና ኢቫን ፔሪሺች በጭንቅላቱ መቶ ለኢንተር ሚላን የግብ ሙከራ አድርገዋል።

ቶኒ ክሮስ በ 17 ደቂቃ ላይ ለሪያል የመክፈቻውን ግብ ሲያስቆጥር ማርኮ አሴንሲዮ በሁለተኛው አጋማሽ በ11 ደቂቃ ላይ በሚያምር አጨራረስ ለባለሜዳው ግብ አስቆጥሯል።

የቀድሞው የጀርመን አማካይ ቶኒ ክሩስ ያስቆጠራት ግብ የላሊጋው ቡድን በአውሮፓ ውድድር ያስቆጠረው 1,000ኛ ጎል ነበር። ይህም ሎስ ብላንኮዎቹ የመጀመሪያው ክለብ ያደርጋቸዋል።

today.in-24.com

የካርሎ አንቸሎቲ ተጫዋቾች ከእረፍት በፊት መሪነታቸውን በእጥፍ ሊያሳድጉ ይችሉ ነበር ፣ ነገር ግን ሮድሪጎ ያደረገው አስደናቂ የግብ ሙከራ የግቡ መአዝን ገጭቶ ተመልሷል።  

ተቀይሮ የገባው አሴንሲዮ ወደ ሜዳ ከገባ ከአንድ ደቂቃ በኋላ ጎል አስቆጥሯል። የክንፍ ተጫዋቹ ኳሱን ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ ተቀብሎ በአስደናቂ አጨራረስ በሳሚር ሃንዳኖቪች መረብ ላይ አስቆጥሯል።

በሁለተኛው አጋማሽ ኢንተር ጨዋታውን ቢቆጣጠሩም አንድም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም። ኒኮሎ ባሬላ በሪያል ማድሪድ ተከላካይ ኤደር ሚሊታኦን ላይ ጥፋት በመስራቱ በ60ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል።

italy24news.com

ሁለቱም ክለቦች ሰኞ ታህሳስ 13 በስዊዘርላንድ ኒዮን በሚካሄደው የ ዩሲኤል የመጨረሻ 16 እጣ ድልድል እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football