Connect with us
Express news


Football

ቼልሲዎች ስድስት ግብ በተቆጠረበት ግጥሚያ ከሴንት ፒተርስበርግ ጋር አቻ ተለያይተዋል!

Chelsea Held to Thrilling Six Goal Draw in Saint Petersburg!
eng.premierliga.ru

ቼልሲዎች ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ወደ ምርጥ 16 አልፈዋል። ዜኒቶች ግጥሚያው 3-3 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ዩሮፓ ሊግ ተቀላቅለዋል።

የአምና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ቼልሲ ረቡዕ በጋዝፕሮም አሬና ከዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ጋር 3-3 በሆነ አቻ ውጤት በመለያየቱ የምድብ ስምንት የመሪነት ዕድሉን አባክኗል።

ውጤቱም የቶማስ ቱቸል ቡድን ፣ በሌላኛው ጨዋታ ማልሞን 1-0 ያሸነፈው እና ከምድብ አሸናፊው ጁቬንቱስ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል።

ቼልሲዎች ቲሞ ቨርነር ሮስ ባርክሌይ ያሻማዉን የማዕዘን ምት በማስቆጠር ገና በ90 ሰከንድ መምራት ችለዋል።

sportingnews.com

ነገር ግን ዜኒት በአውሮፓ ሻምፒዮኑ ቡድን ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር በፍጥነት ሁለት ተከታታይ ግቦችን አስቆጥረዋል።

በመጀመሪያ ክላውዲንሆ በ 38 ደቂቃ በጭንቅላቱ የአቻነት ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ፣ ከሶስት ደቂቃ በሗላ ሳርዳር አዝሙን ማልኮም ያሻገረለትን ኳስ በኬፓ አሪዛባላጋ መረብ ላይ በማሳረፍ ባለሜዳው ቡድን መሪ እንዲሆን አድርጓል

የቱቸል ቡድን ከእረፍት መልስ ተሻሽሎ የቀረበ ሲሆን ፣ ሮሜሉ ሉካኩ በ62 ደቂቃ ቬርነር ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ብድኑን አቻ ማድረግ ችሏል ይህም በመስከረም በዜኒት ግብ ካስቆጠረ በኋላ የመጀመርያ ግቡ ነበር።

skysports.com

ከዚያም ግጥሚያው ሊጠናቀቅ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ቨርነር እንግዳው ቡድን ድጋሚ መሪ ያደረገውን ግብ በሚካሂል ከርዛኮቭን መረብ ላይ አስቆጥሯል።

ሆኖም በተጨማሪ ሰአት ተቀይሮ የገባው ማጎመድ ኦዝዶቭ ዜኒት በድጋሚ አቻ ሲያደርግ ቼልሲዎችን ደግሞ በምድቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥጡ አድርጓል።

ዜኒት አሁን በታህሳስ 13 የሚካሄደውን የኢሮፓ ሊግ የእጣ ድልድልን ይጠባበቃሉ። በተመሳሳይ ቀን ቼልሲዎች በ ዩሲኤል ከማን ጋር እንደሚጫወቱ ያውቃሉ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football