Connect with us
Express news


Football

የታላላቆቹ ቡድኖች ፍልሚያ በባየርን አሸናፊነት ተጠናቋል ፣ ባርሴሎና ወደ አውሮፓ ሊግ ወርዷል!

የታላላቆቹ ቡድኖች ፍልሚያ በባየርን አሸናፊነት ተጠናቋል ፣ ባርሴሎና ወደ አውሮፓ ሊግ ወርዷል!
bavarianfootballworks.com

ባየር ሙኒክ ባርሴሎናን በአሊያንዝ አሬና በቀላሉ አሸንፏል። ሙለር ፣ ሳኔ እና ሙሲላ ለባለሜዳው ቡድን ግብ አስቆጥረዋል!

ባየር ሙኒክ በሜዳው ባርሴሎናን 3-0 በማሸነፍ የላሊጋውን ቡድን ከቻምፒየንስ ሊግ በማስወጣት ወደ አውሮፓ ሊግ አስገብቶታል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ቶማስ ሙለር እና ሌሮይ ሳኔ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ባለሜዳዎቹን ያነሳሱ ሲሆን ጀማል ሙሲላ ባስቆጠራት ጎል ባቫርያኑ ጨዋታውን ገድለው በምድብ 5 የ100% ሪከርድ ማስመዝገብ ችለዋል።

የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 11 ደቂቃ ሲቀረው ሌዋንዶውስኪ ወደ ሳጥን ውስጥ ያሻገረውን ኳስ ሙለር በጭንቅላቱ ገጭቶ በማስቆጠር 50ኛ የዩሲኤል ግቡን አግኝቷል ፣ በዩሲኤል ታሪክ ውስጥም ይህን ያሳካ ስምንተኛ ተጫዋች መሆን ችሏል።

beinsports.com

ባየርን ከእረፍት በፊት በድጋሚ ጎል አግኝቷል ፣ ሳኔ ከ25 ሜትር ርቀት ላይ የሚገርም ግብ አስቆጥሯል። ለማለፍ ማሸነፍ የሚያስፈልጋቸው ካታላኖች በሁለተኛው አጋማሽ ብዙም ሳይሳካላቸው የቀረ ሲሆን ሙሲያላ 62ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሮ መውጣታቸውን አረጋግጧል።

eurosport.com

በምሽቱ ሌላኛው የምድብ ጨዋታ ቤንፊካ ዳይናሞ ኪዪቭን አሸንፎ አዲሱ የባርሴሎና አሰልጣኝ የዣቪ ሄርናንዴዝ ቡድን ከ2004-05 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩሲኤል ምርጥ 16 ውስጥ እንዳይገባ አድርጓል።

በሁለተኛው አጋማሽ አንድም እድል መፍጠር ያልቻለው ባርሴሎና በስድስት የምድብ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ብቻ ያስቆጠረ ሲሆን ፣ ዣቪ ባለፈው ቅዳሜ ከሪያል ቤቲስ ጋር ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

“ባየርን የተሻሉ ፣ የበላይ ነበሩ” ሲል ዣቪ ተናግሯል። “ልንጋፈጠው የሚገባ እውነታ ይህ ነው ለተጫዋቾቼ የነገርኳቸው ይህ የለውጥ ሂደት ነው ዛሬ አዲስ ዘመን መጀመር አለበት ፣ ባርሳን ወደ ሚገባው ቦታ መውሰድ አለብን ይህም አውሮፓ ሊግ አይደለም::

“እኔ ተበሳጭቻለሁ ምክንያቱም ይህ የእኛ እውነታ ነው። እኛ ከባዶ ጀምረናል እና ባርሴሎናን ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መመለስ አለብን። አሁን ኃላፊነት ይሰማኛል። ለጊዜው አውሮፓ ሊግን ማሸነፍ አለብን.”

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football