Connect with us
Express news


Football

ያንግ ቦይስ እና ቀይ ሰይጣኖቹ በቲያትር ኦፍ ድሪምስ አቻ ወጥተዋል!

Young Boys, Red Devils in Theatre of Dreams UCL Draw!
goal.com

የግሪንዉድ ድንቅ ጎል በራይደር ግብ ተጣፍቶ በኦልድትራፎርድ ጨዋታው 1-1 ተጠናቋል። ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ መጨረሻው 16 ሲያልፍ የስዊዘርላንዱ ቡድን ከአውሮፓ ውድድር ውጪ ሆኗል!

ለሙከራ የገባው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን ረቡዕ በኦልድትራፎርድ ባደረገው የመጨረሻ የዩኢኤፍኤ ቻምፒየንስ ሊግ ምድብ 6 ጨዋታ ከያንግ ቦይስ ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ምርጥ የማይባል ብቃት አሳይቷል።

ዩናይትድ በምድቡ አንደኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እርግጠኛ ሲሆን አዲሱ አሰልጣኝ ራልፍ ራንኒክ እሁድ እለት ካደረጉት የመጀመርያ ጨዋታ 11 ለውጦችን አድርጓል አንቶኒ ኢላንጋ እና አማድ ዲያሎ የዩሲኤል የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

የስዊዘርላንዱ ቡድን ቢያሸንፍ ከምድቡ ሶስተኛ ሆነው በማጠናቀቅ አውሮፓ ሊግን እንዲቀላቀል እድል ይሰጠው ነበር። ነገር ግን ዩናይትድ ነበር በተሻለ መልኩ ጨዋታውን የጀመረው እና በ9 ደቂቃ በማይታመን ሁኔታ ሜሰን ግሪንዉድ ሉክ ሾው ያሻማውን ኳስ በአክሮባት መትቶ መሪነቱን አግኝቷል።

thefootyscores.com

ሆኖም ዩናይትዶች መሪነታቸውን በእጥፍ የሚጨምሩባቸውን ኳሶች ሳይጠቀሙ ቀርተው በ42 ደቂቃ ፋቢያን ራይደር ዶኒ ቫን ደ ቢክ ለማቀበል የሞከረውን ኳስ በጥሩ ሁኔታ በማግኘት ግብ ጠባቂው ዲን ሄንደርሰን አሳልፎ አስቆጥሯል።

የዴቪድ ዋግነር ያንግ ቦይስ ያስቆጠሩት ጎል በራስ መተማመናቸውን ያዳበረ ሲሆን ከጥቂት ሰከንዶች በኋላም ሊደግሙ ተቃርበው ነበር ፣ ዩናይትድ ጎል ከገባበት በኋላ ሪትሙን ማግኘት ተስኖት ነበር።

rpp.pe

እንግዶቹ ከእረፍት በኋላ አሸናፊውን ግብ የማግኘት እድል ያለው ቡድን መምሰላቸውን የቀጠሉ ሲሆን ኩዌንቲን ማሴራስ የተሻለ ማድረግ ሲገባው ወደ ውጪ መትቶ ሲወጣ ኢላንጋ ጥሩ ሙከራ በያንግ ቦይስ ግብ ጠባቂ ጊዩም ፋይቭሬ ተመልሶበታል።

ራግኒክ በሁለተኛው አጋማሽ ለግብ ጠባቂው ቶም ሄተን እና አማካዮች ዚዳን ኢቅባል እና ቻርሊ ሳቬጅ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የማድረግ እድል ሰጥቷል።

በዚህ ምድብ በአታላንታ እና ቪላሪያል መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በከባድ በረዶ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። ሆኖም ያ ጨዋታ ዩናይትድ ወይም ያንግ ቦይስ በምድብ 6 ከሚጨርሱበት ቦታ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football