Connect with us
Express news


Football

አርሰናል ሳውዝሃምፕተንን በሚያስተናግድበት ግጥሚያ ሶስት አስፈላጊ ነጥቦችን ማግኘት ይፈልጋል!

Arsenal Welcome Southampton, Seek Three Important EPL Points!
socialtelecast.com

ሳውዝሃምፕተን ለቅዳሜ የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያ ወደ ሰሜን ለንደን ተጉዟል። አርቴታ ጫናዉን ለመቀነስ ማሸነፍ አለበት። ሳውዝሃምፕተን ነጥብ ማግኘት ይፈልጋል። በዚህ አጓጊ ግጥሚያ ላይ ምን ሊከሰት ይችላል?

ማይክል አርቴታ ትከሻ ላይ ጫናው እየጨመረ በመምጣቱ አርሰናል ቅዳሜ ምሳ ሰአት ላይ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሳውዝሃምፕተን ጋር በኤምሬትስ በሚያደርጉት ጨዋታ ወደ አሸናፊነት መመለስ ይፈልጋሉ።

መድፈኞቹ በሳምንቱ አጋማሽ በኤቨርተን 2-1 የተሸነፉ ሲሆን የራልፍ ሃሰንሁትል ቡድን ደግሞ ከብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ጋር አቻ ተለያይቷል።

አርሰናል በዚህ ወር ሁለት ሽንፈትን አስተናግዶ በኢ.ፒ.ኤል. የደረጃ ሰንጠረዥ ወደ ሰባተኛ ደረጃ እንዲወርድ አድርጎታል ፣ ከምርጥ አራትም በአራት ነጥብ ርቆ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳውዝሀምፕተን ካለፉት አራት ግጥሚያዎቹ በ 2ቱ አቻ ተለያይቶ እና በሁለቱ ሽንፈትን አስተናግዶ በደረጃ ሰንጠረዡ በ16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አርሰናሎች ግራኒት ዣካን ከተጠበቀው ጊዜ ቀደም ብለው ከኤቨርተን ጋር በነበራቸው ግጥሚያ ላይ ወደ ቡድኑ ቢመለስም ጋብሪኤል ማርቲኔሊ በደረሰበት ጉዳት ከሜዳ ርቆ የሚቆይ ይሆናል። ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች በህክምናው ሲድ ኮላሲናችን የሚቀላቀል ይመስላል።

ሆኖም አርቴታ የ 21 አመቱ ወጣት ኤሚል ስሚዝ-ሮዌን ባለፈው ሰኞ የመርሲሳይድ ጨዋታ ካመለጠው በኋላ ወደ ቡድኑ እንደሚመልሰው ተስፋ አድርጓል።

independent.ie

የመድፈኞቹ ካፒቴን ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ የባለፈው ግጥሚያ ካመለጠው በኋላ በዚህ ግጥሚያ በምርጥ 11 እንደሚካተት ይጠብቃል።

ሳውዝሃምፕተንን በተመለከተ መሀመድ ሳይልሱ እና ኦሪዮል ሮሜዩ በቅጣት ምክንያት የሚያመልጣቸው ሲሆን ጃክ ስቴፈንስ እና ኢብራሂማ ዲያሎ ተጫዋቾቹን ለመተካት ተዘጋጅተዋል።

ጃን ቤድናሬክ እና ስቱዋርት አርምስትሮንግ ጉዳት ላይ ሲሆኑ ፍራሴር ፎርስተር እና አሌክስ ማካርቲ እንዲሁም በግጥሚያው አይሰለፉም እናም የ40 አመቱ ቪሊ ካባሌሮ ልሴንትስ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

ቲዮ ዋልኮት ምናልባት የቀድሞ ክለቡን በሚገጥሙበት ሰአት በተቀያሪ ወንበር ላይ ሊቀመጥ ይችላል። አርማንዶ ብሮጃ በአጥቂነት ቦታ ገሚሰለፍ ከሆነ ደግሞ አዳም አርምስትሮንግ በተቀያሪው ወንበር ዋልኮትን ሊቀላቀል ይችላል።

skysports.com

አርሰናል በሜዳው እያሳየ ያለው ጠንካራ አቋም እና ሳውዝሃምፕተን ያሳየው ደካማ ጉዞ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፣ መድፈኞቹ በሁለቱ አጋማሽ ግብ አስቆጥረው 2-0 እንደሚያሸንፍ እንጠብቃለን።

የአርሰናል ተጠባቂ አሰላለፍ:

ራምስዴል ፤ ቶሚያሱ ፣ ዋይት ፣ ግብርኤል ፣ ቲየርኒ ፤ ዣካ ፣ ፓርቲ ፤ ሳካ ፣ ኦዲጋርድ ፣ ስሚዝ ሮው ፤ ኦባሚያንግ

የሳውዝሃምፕተን ተጠባቂ አሰላለፍ:

ካባሌሮ ፤ ሊቭራሜንቶ ፣ ሊያንኮ ፣ ስቴፈንስ ፣ ዎከር-ፒተርስ ፤ ሬድሞንድ ፣ ዲያሎ ፣ ዋርድ ፣ ኢሊዩኖሲ ፤ አዳምስ ፣ ብሮጃ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football