Connect with us
Express news


Football

ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ ሊድስ ዩናይትድን አሸነፈ!

Chelsea Edge Past Leeds in Thriller at Stamford Bridge!
vbetnews.com

የጆርጊንሆ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች ቼልሲዎች በስታምፎርድ ብሪጅ ሊድስ ዩናይትድን እንዲያሸንፉ አድርገዋል። ራፊንሃ እና ጌልሃርት ለእንግዳው ቡድን ግብ አስቆጥረዋል!

ቅዳሜ እለት በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 3-2 ሲያሸንፍ ጆርጊንሆ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያዉን ግብ አስቆጥሯል።

ቼልሲዎች በዌስትሀም ዩናይትድ ከተሸነፉ እና ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በቅርቡ አቻ ከተለያዩ በኋላ ድሉ ለቼልሲ ወሳኝ ነበር።

የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱቸል ከጨዋታው በኋላ “ጥሩ የእግር ኳስ ጨዋታ ነበር። በጣም ከባድ ግጥሚያ ነበር እና ባሳየነው አቋም በጣም ደስተኛ ነኝ” ብሏል።

“ማሸነፍ ይገባናል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን በተጨማሪ ሰአት ዘግይተህ ጎል ማስቆጠር መታደል ነው። ሆኖም ሁለት ጊዜ ከኋላ ተነስተን ማሸነፋችን በጣም አስደናቂ ነው እና በጣም ደስተኛ ነኝ። እንደጠበቅነው ከባድ ስራ ነበር።”

” በግጥሚያው እድለኞች ነበርን ፣ ሆኖም ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ዘግይተን ጎል በማስተናገዳችን እድለኞች አልነበርንም ፤ ስለዚህ ምናልባትም ይህ ድል በጣም የምንፈልገው ነገር ሊሆን ይችላል” ሲል የሰማያዊዎቹ አለቃ ተናግሯል።

ማርኮስ አሎንሶ በ28 ደቂቃ ላይ በሰራው ጥፋት እንግዳው ቡድን ፍፁም ቅጣት ምት ያገኘ ሲሆን ራፊንሃም እድሉን ወደ ግብ በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል።

si.com

ሆኖም የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 3 ደቂቃ ሲቀረው ሜሰን ማውንትን አሎንሶ ያሻማለትን ዝቅተኛ ኳስ በቦታው ላይ ባልነበረው የሊድስ ግብ ጠባቂ ኢላን ሜስሊየር መረብ ላይ አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል።

ከዚያም ራፊንሃ በግብ ክልል ውስጥ በአንቶኒዮ ሩዲገር ጥፋት የሰራ ሲሆን ፣ ጆርጊንሆም በ58ኛው ደቂቃ እድሉን ወደ ግብ በመቀየር ቼልሲን ቀዳሚ አድርጓል።  

mealmadrid-futbol.com

ተቀይሮ የገባው ጆ ጌልሃርድት በመጀመሪያ ንክኪው ጎል አስቆጥሮ ቡድኖቹን አቻ ማድረግ ቢችልም ቼልሲዎች በተጨማሪው ደቂቃ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷቸው ጆርጊንሆ በድጋሚ ጎል አስቆጥሯል።

eurosport.com

“ሶስት ነጥቦች ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነበር። ከባድ ጨዋታ ነበር ፣ ሊድስ ከባድ ተጋጣሚ ናቸው ነገር ግን ድሉ ይገባናል። የመጨረሻው ደቂቃ ጎል በጣም አስደናቂ ነበር። በስታዲየሙ የተገኘ ሁሉም ሰው በጣም ጥሩ ስሜት ተሰምቶታል። ” ሲል ጆርጊኖ ተናግሯል።

ቼልሲ በኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዡ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሊድስ በ16 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football