Connect with us
Express news


Football

አስደናቂው አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም ሳውዝሃምፕተንን አሸነፈ!

Awesome Arsenal Sink Southampton at the Emirates!
sportskeeda.com

ኦባሚያንግ ባልተገለጸ “የዲሲፕሊን ጥሰት” ምክንያት በግጥሚያው አለመካተት የአርቴታ ተጫዋቾች በሰሜን ለንደን ሳውዝአምፕተንን ከማሸነፍ አላገዳቸውም!

ቅዳሜ እለት አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሳውዝሃምፕተንን 3-0 ሲያሸንፍ በሜዳውm ሆነ ከሜዳው ውጪ ድራማዎችን ተቋቁሟል ፣ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ የፊት መስመር ተጫዋቹ ኦባሚያንግን ሳይዝ ገብቷል።

ከጨዋታው በፊት አርቴታ እንደተናገረው ፣ የክለቡ ካፒቴን በግጥሚያው ያልተካተተው “በዲሲፕሊን ጥሰት” ምክንያት እንደሆነ ሲገልጽ አሌክሳንደር ላካዜት ብቸኛ አጥቂ ሆኖ ተጫውቷል።

ሳውዝሀምፕተን በዝናባማው የከሰአት የኤሚሬትስ ጨዋታ አዳም አርምስትሮንግ ባደረገው አስደናቂ የመአዝን ምት የግብ ሙከራ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል።

ሆኖም ባለ ሜዳው ቡድን የሴንቶች የማጥቃት ጫና በመስበር እና ጥሩ የኳስ ቅብብል በማድረግ ፣ አሌክሳንደር ላካዜት በግራ መስመር ቡካዮ ሳካ ያቀበለውን ኳስ ወደ ላይኛው ጥግ በመምታት በ21ኛው ደቂቃ የመክፈቻዉን ግብ አስቆትሯል።

thesun.co.uk

የአርቴታ ተጫዋቾች ፣ ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ ኦዲጋርድ የሳውዝሃምፕተን ተከላካዮች በተዘናጉበት ሰአት ግብ አስቆጥሮ መሪነታቸውን እጥፍ አድርገዋል። ኖርዌያዊው ተጫዋች ፣ ስኮትላንዳዊው የግራ ተመላላሽ በጭንቅላቱ ያሻማለትን ኳስ ወደ ግብ መቀየር ችሏል።

thesun.co.uk

ግቡ ለኦዲጋርድ በሶስት የኢ.ፒ.ኤል ጨዋታዎች ሶስተኛው ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ጥሩ የኳስ ቅብብል በማድረግ የሳውዝሃምፕተንን የተከላካይ መስመር ሲያጨናንቅ ነበር።

ሁለተኛው ግብ የሳውዝሃምፕተኖች በራስ መተማመን የቀነሰ ሲሆን የተከላካይ መስመራቸው ጥንካሬም አደብዝዟል።  የአርሰናሉ ተከላካይ ጋብሪኤል በ60 ደቂቃ ላይ ሶስተኛውን ግብ ያስቆጠረ ቢሆንም ፣ ግቡ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ተሰርዟል።

ሆኖም ብራዚላዊው ተጫዋች ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ ብቅ በማለት ከማእዘን የተሻማውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት 3-0 እንዲያሸንፉ አድርጓል።

reuters.com

አርምስትሮንግ እና የግብ ባልደረባው አርማንዶ ብሮጃ በጉዳት ከሜዳ በመውጣታቸው ምክንያት ሳውዝሃምፕተኖች በሁለተኛው አጋማሽ ምንም አይነት እድሎችን ለመፍጠር ሲቸገሩ ታይተዋል።

ከቅዳሜው ውጤት በኋላ ድሉ አርሰናልን በ26 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጥ የራልፍ ሃሰንሁትል ሳውዝሃምፕተን ደግሞ በ16 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football