Connect with us
Express news


Football

ፒኤስጂ ሞናኮን በቀላሉ ባሸነፈበት ግጥሚያ ምባፔ ሁለት አስደናቂ ግቦችን አስቆጥሯል!

PSG Ease Past Monaco, Mbappé Nets Sensational Double!
new.in-24.com

ፒኤስጂ እሁድ እለት በሊግ 1 ሞናኮን አሸነፈ። ሌ ፓሪሴንስ ድል ሲያስመዘግቡ ምባፔ ሁለት ግብ አስቆጥሯል።

የማውሪሲዮ ፖቸቲኖው ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የሊግ 1 ሻምፒዮን ለመሆን በሚያደርጉት ጉዞ ፣ ኪሊያን ምባፔ በኤኤስ ሞናኮ መረብ ላይ ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ በሜዳቸው 2-0 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፉ አድርጓል።

ምባፔ በመጀመሪያዎቹ 45 ደቂቃዎች በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ግብ አስቆጥሮ የሊጉን መሪ ከ18 ጨዋታዎች 45 ነጥብ በመሰብሰብ እና አንድ ቀሪ ጨዋታ ካለው ማርሴይ በ13 ነጥብ በልጦ እንዲቀመጥ አድርጓል።

በአሰልጣኝ ኒኮ ኮቫች የሚመራው ሞናኮ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎቹን በማሸነፍ በ26 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሞናኮዎች በስድስት ነጥብ ብቻ ርቀው ለሁለተኛ ደረጃ ከሚፋለሙት 6 ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን ስታድ ሬኔስ በ31 ነጥብ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በመጨረሻ ግጥሚያው በሜዳው 4ኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ኒስ የ2-1 ሽንፈት አስተናግዷል።

በቀድሞው ክለቡ ላይ በ10 ጨዋታዎች ዘጠነኛ እና 10ኛ ጎሉን ያስቆጠረው ምባፔ “አሳማኝ ውጤት ላይሆን ይችላል ነገር ግን ግጥሚያውን በመጀመሪያው አጋማሽ ገድለን ወጥተናል” ብሏል።

fotmob.com

ሞናኮዎች በፓርክ ዴ ፕሪንስ በጥሩ ሁኔታ የጀመሩ ሲሆን አማካዩ ሶፊያን ዲዮፕ በሁለተኛው ደቂቃ ያደረገውን አስደናቂ ሙከራ የግቡ ማእዝን የመለሰለት ሲሆን ለፒኤስጂው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ የተመለሰውን ኳስ በቀላሉ ተቆጣጥሮታል።

ሆኖም ሌ ፓሪሲየንስ የፍፁም ቅጣት ምት ለማስቆጠር 12 ደቂቃ ብቻ የፈጀባችቸው ሲሆን ምባፔ ተከላካዩ ጂብሪል ሲዲቤ በኤንጂል ዲማሪያ ላይ በሰረአው ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብ መቀየር ችሏል።

sportskeeda.com

ክሊያን ምባፔ በከፍተኛ ፍጥነት በመልሶ ማጥቃት መሪነቱን በእጥፍ ያሳደገ ሲሆን ፈረንሳዊው ተጫዋች ዲ ማሪያ ያሻገረለትን ኳስ ከምረብ ጋር በማሳረፍ በውድድር ዘመኑ ዘጠነኛው የሊግ 1 ጎቡን አግኝቷል።

ሞናኮዎች የግብ ልዩነቱ የሚቀንስባቸው በርካታ እድሎች ቢያገኙም ፒኤስጂዎች በሊግ 1 ሁለት አስጨናቂ ጨዋታዎች ካሳለፉ በኋላ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ጥሩ አቋም አሳይተዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football