Connect with us
Express news


Football

በማንቸስተር ውስጥ በተደረገ አስደናቂ ጨዋታ ሲቲ ሊድስ ላይ ሰባት አስቆጥሯል!

Madness in Manchester as Sensational City Smash Seven Past Leeds!
standard.co.uk

ሊድስ ዩናይትድን በአጠቃላይ የበላይነት በቀጠቀጡበት ጨዋታ ዴ ብሩይን ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር የቡድን አጋሮቹ አምስት ተጨማሪ አስቆጥረዋል። የጋርዲዮላ ቡድን በፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሆኖ ይቆያል!

ማንቸስተር ሲቲ ማክሰኞ እለት በኢትሃድ ሊድስ ዩናይትድን 7-0 በማሸነፍ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የሚመራበትን ልዩነት አስፍቷል።

ባለሜዳዎቹ በፍጥነት ጨዋታውን የተቆጣጠሩት ሲሆን ፊል ፎደን ፣ ጃክ ግሬሊሽ እና ኬቨን ደብሩይነ ያስቆጠሯቸው ጎሎች እረፍት ከመውጣታቸው በፊት የሶስት ጎል መሪነት ሰጥቷቸዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ሪያድ ማህሬዝ አራተኛውን ለሲቲ አስቆጥሯል ፣ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ የሞከረው ኳስ ጁኒየር ፊርፖን ገጭቶ የሊድሱን ግብ ጠባቂ ኢላን ሜስሊየር አልፎ ገብቷል።

ሲቲዝንስ ኳሱን ከሊድስ በራሳቸው አጋማሽ ከነጠቁ በኋላ ዴ ብሩይን ከሩቅ መትቶ በማስቆጠር ቡድኑ 5-0 በሆነ ውጤት ጨዋታውን እንዲመራ አድርጓል።

telegraph.co.uk

ጆን ስቶንስ ለሲቲ በ74ኛው ደቂቃ ስድስተኛውን ግብ ከመረብ በማሳረፍ ሊድስን በኢ.ፒ.ኤል. ታሪኩ ውስጥ ትልቁን ሽንፈት አከናንቦታል።

ከዚህ ጨዋታ በፊት በእንግሊዝ ከፍተኛ ሊግ የሊድስ ትልቁ ሽንፈት በ1995-96 በሊቨርፑል 5-0 የተሸነፈበት ጨዋታ ነበር።

የሊድስ አለቃ ማርሴሎ ቢኤልሳ “ከእኛ አፈፃፀም የሚወሰድ ምንም አዎንታዊ ነገር የለም” ብሏል። “እኔ ዋጋ ሊሰጠው የሚችል ምንም ነገር ማግኘት አልቻልኩም ፣ ጥሩ የተሰራ ነገር ከሌለ ፣ እያንዳንዱ ተጫዋች አይደለም የሚወቀሰው ፣ ግን አመራር እና አደረጃጀት ነው። እኔ ማቅረብ የምችለው ምንም ምክንያት የለም።”

ሲቲዎች በዛ አላበቁም ፣ ናታን አኬ ከማእዘን የተሻገረለትን ኳስ አግኝቶ ሜስሊየርን አሳልፎ በማስቆጠር ለቢኤልሳ ቡድን ውርደቱን ጨምሯል።

standard.co.uk

“ለሁሉም ሰው ጥሩ ነው ፣ ምናልባት ብዙ ያልተጫወቱ ብዙ ተጫዋቾች ዛሬ ተጫውተዋል እናም አስተዋፆ አድርገዋል።ለቡድኑ በሙሉ አበረታች ነው።”

ሲቲ በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ካለው ሊቨርፑል በአራት ነጥብ በልጦ ፣ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ካለው ቼልሲ በአምስት ከፍ ያለ ሲሆን የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ከአሳዳጆቹ ሁለቱ ቡድኖች አንድ ተጨማሪ ጨዋታ አድርጓል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football