Connect with us
Express news


Football

ኤቨርተን በስታምፎርድ ብሪጅ ከአንድ ለባዶ መመራት ተነስቶ ከቼልሲ ጋር አቻ ተለያይቷል!

Everton Fight Back from One Down to Hold Chelsea at Stamford Bridge!
inkhel.com

ቼልሲዎች ማውንት ያስቆጠረው ግብ በብሬንዝዌት ከተሰረዘ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ ከመሪው ቡድን ጋር የነበራቸው የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል አምክነዋል።

ቼልሲዎች በሁለተኛው አጋማሽ የነበራቸውን መሪነት አጥተው ከምዕራብ ለንደኑ ኤቨርተን ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት በመለያየታቸው ፣ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተቀናቃኛቸውን ማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ጋር የነበራቸውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድሉን አባክነው።

ባለኤዶቹ የቶማስ ቱቸል ተጫዋቾች ብዙ የግብ እድሎችን ካባከኑ ፣ ግጥሚያው ሊጠናቀቅ 20 ደቂቃ ሲቀረው ሜሰን ማውንት በፒክ ፎርድ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ አማካኝነት መሪ መሆን ችለው ነበር። ሆኖም ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ታዳጊው ተከላካይ ጃራድ ብራንትዋይት ቡድኑን አቻ አድርጓል።

ቼልሲዎች ከመጀመርያው ጨዋታ ጀምረው የተሻሉ ቡድን ነበሩ እና ቀድሞውንም መሪነት ለመውሰድ ቢቃረቡም ፣ ፒክፎርድ የክርስቲያን ፑሊሲች ፣ ሃኪም ዚዬች እና ጄምስ ከ25 ያርድ ያደረጓቸውን ሙከራዎች ከማዳኑ በፊት ፣ ሬይስ ጀምስ እና ማውንት በጥሩ ቦታ ላይ ያገኟቸውን መልካም የግብ እድሎችን ወደ ውጪ አውጥተዋል።

ነገርግን የእንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ በመክፈቻው አጋማሽ ያዳነውን ርጥ ኳስ በ35ኛው ደቂቃ የተገኘ ሲሆን ፣ የአገሩ ልጅ ሜሰን ማውንት ከሩዲገር የተላከለትን ኳስ ከቀርብ ርቀት ቢመታውም ግብ ጠባቂው በቀኝ እግሩ ኳሱን አድኖታል።

ሜሰን ማውንት በ70 ደቂቃ የመክፈቻውን ግብ አስቆጥሯል። ማውንት በፈጣን መልሶ ማጥቃት ከጄምስ የተሻገረለትን ኳስ በፒክፎርድ መረብ ላይ በማስቆጠር ቼልሲዎች ቀዳሚ አድርጓል።

thesun.co.uk

ነገር ግን ከአራት ደቂቃዎች በኋላ አንቶኒ ጎርደን ያሻማዉን ቅጣት ምት ታዳጊው ብራንዝዋይት ወደ ግብ በመቀየር በውድድር አመቱ በመጀመርያው የኢ.ፒ.ኤል. ተሳትፎው የመጀመርያ ግቡ አስነዝግቧል።

eurosport.com

ቼልሲዎች የማሸነፊያ ግብ ቢፈልጉም በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ያሳዩትን አጨዋወት መድገም አልቻሉም። ቲያጎ ሲልቫ መሪነቱን ለመመለስ ጥሩ እድል አግኝቶ ነበር ነገር ግን ፒክፎርድንም ማለፍ አልቻለም ብራዚላዊው በግንባሩ የመታዉን ኳስ በጥሩ ሁኔታ አውጥቶታል።

ከውጤቱ በኃላ ቼልሲዎች በኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዥ ፣ ከመሪው ማንቸስተር ሲቲ በ4 ነጥብ ዝቅ ብለው በ37 ነጥብ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የአሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ኤቨርተን 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

youtube.com

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football