Connect with us
Express news


Football

አስደናቂው ሲቲ ኒውካስልን በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ ከፍተኛዉን ደረጃ ላይ ተቀምጦ ገናን ያከብራል!

Stunning City Outclass Newcastle to Stay Top for Christmas!
theflashportal.in

ማንቸስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ሌላ ጎል የሞላበት እንቅስቃሴ አሳይቷል። ኒውካስል ለሲቲ ኮከቦች ምላሽ መስጠት አልቻሉም እና በአደጋኛው ​ቀጠና ውስጥ ይቆያሉ!

ማንቸስተር ሲቲ እሁድ በሴንት ጀምስ ፓርክ ኒውካስትል ዩናይትድን 4-0 በማሸነፍ በገና ቀን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል) የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ሆኖ ይቆያል።

በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ውስጥ የመሀል ተከላካዩ ሩበን ዲያስ እንዲሁም ጆአዎ ካንሴሎ ፣ ሪያድ ማህሬዝ እና ራሂም ስተርሊንግ ባስቆጠራቸው ጎሎች ሲቲዎቹ ፣ ምንም አይነት ነጥብ ማግኘት ተስኗቸው የኢ.ፒ.ኤል የህልውና ጥያቄያቸውን መመለስ ያልቻሉት የኤዲ ሃው ኒውካስትሎችን በቀላሉ እንዲያሸንፉ አድርገዋል።

የእሁዱ ውጤት ሲቲ በተከታታይ ሰባተኛ የሊግ ድል ሲሆን ይህም ከጥቅምት ወር የጀመረ አስደናቂ ጉዞ ነው። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን እስካሁን ካደረጋቸው 18 ጨዋታዎች 44 ነጥብ ሰብስቧል።

ዲያስ የኒውካስል ተከላካይ ሲያራን ክላርክ በሰራው ስህተት በአምስት ደቂቃ ውስጥ ጎል አስቆጥሯል። የአየርላንድ ሪፐብሊክ ተጫዋች በስድስት ያርድ ውስጥ የተሻማዉን ኳስ ማውጣት ባለማቻሉ ፣ ፖርቹጋላዊው የመሀል ተከላካይ በጭንቅላቱ እንዲያስቆጥር አስችሎታል።

sport.aktualne.cz

ካንሴሎ ከ30 ደቂቃ በፊት የሲቲ እድልን በእጥፍ አሳድጎታል። ተከላካዩ በኒውካስትል የግብ ክልል ከ18-ያርድ በመምታት አስደናቂ የሆነ ግብ አስቆጥሯል።

ማህሬዝ በ64 ደቂቃ ላይ ዚንቼንኮ ያሻማለትን ኳስ አየር ላይ እያለ በመምታ የሲቲ ሶስተኛ ግብ አስገኝቷል። ግቡ መጀመሪያ ላይ በመስመር ዳኛ ከጨዋታ ውጪ ተብሎ ነበር ፣ ነገር ግን በቫር ከታየ በኋላ ውሳኔው ተሽሯል።

andina.pe

ስተርሊንግ ሊጠናቀቅ አራት ደቂቃ ሲቀረው ጋብሬል ጂሱስ ያሻገረለትን ዝቅተኛ ኳስ ወደ ግብ በመቀየር የሲቲ የማሳረግያ ግብ አስገኝቷል።

ኒውካስትል በኢ.ፒ.ኤል. የደረጃ ሰንጠረዥ በ10 ነጥብ 19 ደረጃ ላይ ቀጥሏል። የመጨረሻው ደረጃ ላይ የሚገኘው ኖርዊች ሲቲ አንድ ጨዋታ በእጁ የያዘ ሲሆን በቦክሲንግ ደይ አርሰናልን ሲገጥም ማግፒዎችን የመብለጥ እድል አላቸው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football