Connect with us
Express news


Football

ቼልሲ በቪላ ድል በተቀዳጀበት ግጥሚያ ሉካኩ ግብ አስቆጥሯል።

Lukaku on Fire in Chelsea Triumph at Villa!
israel.on-24.com

በግዙፉ የቦክሲንግ ዴይ ፍልሚያ ሰማያዊዎቹ በቀላሉ ባሸነፉበት ግጥሚያ ቤልጂየማዊው አጥቂ አንድ ግብ ሲያስቆጥር አንድ ፍፁም ቅጣት ምት ደግሞ አሸንፏል። ድሉ የቱቼል ተጫዋቾችን በዋንጫ ፉክክር ውስጥ እንዲቆዩ አድርጓል!

አጥቂው ሮሜሉ ሉካኩ በእሁዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ ከሜዳው ውጪ የስቴቨን ጄራርድ አስቶንቪላ 3-1 ባሸነፈበት ግጥሚያ ግብ በማስቆጠር ቡድኑ ወደ ዋንጫው ፉክክር እንዲመለስ አድርጓል።

የቶማስ ቱቸል ቡድን ቀደም ሲል ባደረጋቸው አራት የኢፒኤል ጨዋታዎች አንድ ድል ብቻ ያሳካ ሲሆን ቼልሲዎች በሚድላንድስ ወሳኝ ድል በመቀዳጀት ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል።

ቪላዎች በአጥቂያቸው ኦሊ ዋትኪንስ በግራ በኩል እና በ18 ያርድ ርቀት ውስጥ ብዙ ጊዜ ጫና በመፍጠር በመጀመርያ ደቂቃዎች ውስጥ የተሻሉ ቡድን ሆነው ቢታዩም አንድም ግብ ማስቆጠር ግን አልቻሉም።

ባለ ሜዳው ቡድን በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች በፈጠሩት ጫና ሬስ ጀምስ በራሱ መረብ ላይ ጎል እንዲያስቆጥር አድርገዋል። የቪላ የግራ መስመር ተከላካዩ ማት ታርጌት ያሻማዉን ኳስ የጄምስ ጭንቅላትን በመግጨት በግብ ጠባቂ ኤዶዋርድ ሜንዲን መረብ ላይ አርፏል።

expressandstar.com

ጆርጊንሆ በፍጹም ቅጣት ምት ጎል እንግዳው ቡድንን በ 34 ደቂቃ አቻ ማድረግ ችሏል ፣ ፍፁም ቅጣቱም ተከላካዩ ማቲው ካሽ በአጥቂው ካሉም ሁድሶን ኦዶይ በሰራው ጥፋት የተገኘ ነበር።

ሉካኩ በእረፍት ሰአት ከተጠባባቂ ወንበር ገብቶ ልዩነቱ ፈጣሪ መሆኑን አሳይቷል። ቤልጄማዊው ከሀድሰን-ኦዶይ የተሻገረለትን ድንቅ ወደ ግብ በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል።

besoccer.com

ሜሰን ማውንት የተጋጣሚው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በማታለል ያገኘውን መልካም የግብ ዕድል ወደ ግብ መቀየር ባለመቻሉ የቼልሲዎችን መሪነት የማስፋት ዕድል አምክኗል።

ሉካኩ በባከነ ሰአት በቪላው ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳ በተሰራበት ጥፋት ቼልሲዎች ሁለተኛ ፍፁም ቅጣት ምት እንዲያገኙ ያስቻለ ሲሆን ፣ ጆርጊንሆ የተገኘውን እድል በጥሩ ሁኔታ ወደ ግብ መቀየር ችሏል።

“እንዲህ አይነት ብቃት ያስፈልገኝ ነበር። ወደ ጨዋታ መመለስ በጣም ከባድ ነበር። ጠንክሬ መስራቴን ግን አላቆምኩም ነበር። በአቋሜ በጣም ደስተኛ ነኝ እናም ወደፊት መግፋት አለብኝ።” ሲል የሰማያዊዎቹ አጥቂ ተናግሯል።

ቼልሲ ከመሪው ማንቸስተር ሲቲ በ6 ነጥብ ርቆ በኢ.ፒ.ኤል. የደረጃ ሰንጠረዥ 3ኛ ሆኖ ይቀጥላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቪላ 18 ጨዋታዎችን አድርጎ በ22 ነጥብ ወደ 11ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football