Connect with us
Express news


Football

ሳንቼዝ ዘግይቶ ያስቆጠረው ግብ ለስፐርስ ወሳኝ ድል አስገኝቷል!

Sánchez Strikes Late in Important Spurs Triumph at Watford!
football365.com

ዋትፎርድ በአስደናቂ ሁኔታ ታግሎ ነበር ነገር ግን ዳቪሰን ሳንቼዝ በ96ኛው ደቂቃ የሆርኔቶችን መረብ ማግኘት ችሏል።

ቶተንሃም ሆትስፐር በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ 4 ውስጥ ለመጨረስ የሚያደርገው ጥረት በዳቪንሰን ሳንቼዝ አስደናቂ የተጨማሪ ሰአት ግብ ዋትፎርድን በማሸነፍ ተጠናክሯል።

በጨዋታው ስፐርሶች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢኖራቸውም አጨራረስ ያነሳቸው የአንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቾች ግብ ለማግኘት እስከ ተጨማሪ ሰአት ስድስት ደቂቃ እንዲጠብቁ ተገደዋል ፣ ከዛ ግን ኮሎምቢያዊው ተከላካይ ዴቪንሰን ሳንቼዝ ከሶን ሄንግ ሚን የተሻገረውን ቅጣት ምት አግኝቶ በጭንቅላቱ አስቆጥሯል።

new.fr-24.com

ቀደም ብሎ ሰርጂዮ ሩጊይሎን በ25ኛው ደቂቃ የሞከረው ኳስ በዋትፎርዱ ግብ ጠባቂ ዳንኤል ባችማን የተመለሰ ሲሆን ሃሪ ኬን በመጀመርያ ደቂቃዎች ላይ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወጥቶበታል።

uk.news.yahoo.com

ከእረፍት በኋላ ባችማን ብዙ ስራ ነበረበት። ኦስትሪያዊው በ52 ደቂቃ ላይ ሉካስ ሙራ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ያወጣ ሲሆን የሶንን የቅርብ ርቀት ሙከራም ጨዋታው ሊጠናቀቅ 19 ደቂቃ ሲቀረው አድኗል።

ሳንቼዝ ወሳኟን ጎል ያስቆጠረው በረዥም ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ ሲሆን ይህም የሆነው በቪካሬጅ ሮድ ከተመልካቾች መካከል በደረሰ የህክምና ችግር ምክንያት በመዘግየቱ ነው።

dailymail.co.uk

የስፐርስ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ለስፐርስ ቲቪ እንደተናገሩት “ጨዋታው ከባድ ነበር ምክንያቱም በሚገባ በመከላከሉ ከተደራጀ ቡድን ጋር ተጫውተናል ፤ ይህን አይነት ጨዋታ ተዘጋጅተውበት ነበር ነገርግን ጨዋታውን ተቆጣጥረናል” ሲሉ ተናግረዋል። ብዙ የኳስ ቁጥጥር ነበረን እና የጎል እድሎችን ፈጥረናልን ግን የመጨረሻውን ቅብብል አምልጦናል ብዬ አስባለሁ – የተሻለ መስራት እንችላለን – እንዲሁም በዚህ አይነት ጨዋታ ጎል ቀድመህ ካስቆጠርክ ተጋጣሚህ እቅዱን መቀየር ይኖርበታል። እና ያኔ ቦታ ማግኘት ይቻላል።”

ኮንቴ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶን በህዳር ወር ከተካ በኋላ በአሰልጣኝነት ያለመሸነፍ አጀማመሩን ወደ ስምንት ጨዋታዎች አራዝሟል። ስፐርስ አሁን በኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዥ 6ኛ ላይ ተቀምጧል ነገርግን ሁለት ጨዋታዎች ይቀሩታል ፣ አርሰናል እና ዌስትሃም አራተኛ እና 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በኢፒኤል ከህዳር 20 የጀመረው የዋትፎርድ ድል አልባ ጉዞ ቀጥሏል። የክላውዲዮ ራኒየሪ ሆርኔትስ በ13 ነጥብ ብቻ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

youtube.com

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football