Connect with us
Express news


Football

ቼልሲ እና ሊቨርፑል በዋና ከተማው አቻ ተለያይተዋል!

Classic in the Capital as Chelsea Draw with Liverpool!
niceinfo.xyz

ቀያዮቹ ማኔ እና ሳላህ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ቼልሲዎች ኮቫቺች እና ፑሊሲች ባስቆጠሯቸው ግቦች ከመመራት ተነስተው አቻ መለያየት ችለዋል!

ቼልሲዎች እሁድ በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) አስገራሚ ጨዋታ ከ2-0 መመራት ተነስተው ከሊቨርፑል ጋር አቻ በመውጣት ነጥብ ተጋርተዋል።

የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ በኮቪድ-19 ምክንያት በጨዋታው ላይ ሳይገኙ የቀሩ ሲሆን የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱቸል ደግሞ ቤልጄማዊው የ97.5 ሚ.ፓ ሪከርድ ፈራሚያቸው ሮሜሉ ሉካኩን በሰጠው አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ ከጨዋታ ውጪ ሆነዋል።

እንግዶቹ ጨዋታውን በድምቀት የጀመሩ ሲሆን በመክፈቻው ደቂቃ በሴሳር አዝፒሊኩዌታ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ብቻ በማግኘቱ እድለኛ የሆነው ሳዲዮ ማኔ ትሬቮህ ቻሎባህ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ ቀያዮቹን በ9ኛው ደቂቃ ቀዳሚ እንዲሆኑ አድርጓል።

liverpooloffside.sbnation.com

የመሐመድ ሳላህ የግል ጥረት ሊቨርፑልን በግማሽ ሰአት ውስጥ 2-0 እንዲመራ አድርጎታል ፣ ከአሌክሳንደር አርኖልድ የተሻማለትን ኳስ በአስደናቂ ሁኔታ አስቆጥሯል።

ቼልሲዎች የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ትንሽ ደቂቃዎች ሲቀሩት ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ። ክርስቲያን ፑሊሲች በተጨማሪ ሰዓት የአቻነት ግብ ከማስቆጠሩ በፊት ፣ ማቲዎ ኮቫቺች በ42 ደቂቃ የአየር ላይ ኳስ በካኦኢምሂን ኬሌሄር መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

cbssports.com

አጓጊ በሆነው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች በሁለተኛው አጋማሽ የማሸነፍ እድሎችን ያገኙ ሲሆን የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ የሳላህ እና ማኔ ግሩም ሙከራዎች ሲያከሽፍ ኬሌሄር ደግሞ የፑሊሲች አስደናቂ ሙከራ አድኗል።

ውጤቱ ቼልሲ (43 ነጥብ) እና ሊቨርፑል (42 ነጥብ) በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል። ምንም እንኳን ቀያዮቹ ከማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ ጋር ሲነፃፀሩ አንድ ጨዋታ ቢቀራቸውም የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ሰማያዊዎቹን በ10 ነጥብ በልጦ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ በመቀመጥ የሻምፒዮንነት ፉክክሩን ተቆጣጥሯል።

youtube.com

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football