Connect with us
Express news


Football

ማንቸስተር ዩናይትዶች ማውቲንሆ ዘግይቶ ባስቆጠረው ግብ በሜዳቸው ተሸንፈዋል።

Moutinho Late Strike Sinks Manchester United!
realmadrid-futbol.com

ዎልቨርሃምፕተን ዋንደርደርስ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ተጉዘው ከአርባ አመታት በሁላ የመጀመሪያ ድላቸውን ይዘው ተእልሰዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰኞ እለት በሜዳው በዎልቨርሃምፕተን ዋንደርደርስ 1-0 ተሸንፎ በጊዜያዊ አሰልጣኝ ራልፍ ራንግኒክ ስር የመጀመርያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በ82ኛው ደቂቃ ጆዋ ማውቲንሆ ያስቆጠራት ጎል ዎልቭስ ከ1980 በኋላ በኦልድትራፎርድ የመጀመሪያ ድላቸውን እንዲያገኝ ያስቻለ ሲሆን የብሩኖ ላጅንን ቡድን በ ኢፒኤል የደረጃ ሰንጠረዥ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

ዩናይትዶች ደካማ እንቅስቃሴን ተከትሎ ፣ አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አርሰናል በ አራት ነትብ ዝቅ ብለው በ31 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ዎልቭስ በመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ የግብ እድሎችን መፍጠር ቢችልም ሽልማታቸውን ማግኘት የቻሉት ጨዋታው ሊጠናቀቅ ስምንት ደቂቃዎች ሲቀሩት ሲሆን ማውቲንሆ ፣ ፊል ጆንስ በግንባሩ ገጭቶ ያወጣዉን ኳስ በመምታት በዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ መረብ ላይ አስቆጥሯል።

g3.football

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ራግኒክ በመጀመሪያ ለማስተዋወቅ የሞከሩት ከፍተኛ ጉልበት ያለው ጨዋታ ምንም አይነት ለውጥ ማምጣት አልቻለም።

ጆንስ ከረጅም ጉዳት በኋላ በሁለት አመታት ውስጥ የመጀመርያውን የኢፒኤል ጨዋታ ያደረገው ሲሆን ጊዜያዊ አለቃው ቪክቶር ሊንደሎፍ ፣ ሃሪ ማጉየር እና ኤሪክ ባይሊ በሌሉበት ሰአት የቀድሞ የእንግሊዝ ተከላካይ የመሰለፍ ዕድል አግኝቶ ነበር።

የ29 አመቱ ተጫዋች በኝባሩ ገጭቶ ለማውንቲንሆ ለግብ የሚሆን ኳስ ከማቀበሉ በፊት በጨታው ጥሩእንቅስቃሴ አድርጓል።

espn.com

ዎልቭስ ከእረፍት በፊት በቀላሉ መሪ መሆን ይችል የነበረ ሲሆን ዳንኤል ፖደንስ ፣ ሩበን ኔቭስ እና ኔልሰን ሴሜዶ ያደረጓቸውን አስደናቂ ሙከራዎች ግብ ጠባቂው ማለፍ አልቻሉም።

ባለሜዳው ቡድን ጥቂት የግብ አጋጣሚዎች የፈጠረው ሲሆን በመጀመሪያው አጋማሽ ኤዲሰን ካቫኒ ለሜሰን ግሪንዉድ መስጠት የሚገባዉን ኳስ አምክኗል።

ግሪንዉድ የቀያይ ሰይጣኖቹ ምርጥ ተጫዋች የነበር ሲሆን በብሩኖ ፈርናንዴስን ተቀይሮ በሚወጣበት ጊዜ በሜዳው የተቃውሞ ድምፆች ተሰምተዋል።

ከዚያም ማውቲንሆ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ስምንት ደቂቃ ሲቀረው በዴቪድ ዴሂያ መረብ ላይ ግብ በማስቆጠር ደጋፊዎቹን አስፈንጥዧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football