Connect with us
Express news


EFL Cup

አርሰናል እና ሊቨርፑል በኢኤፍኤል ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይገናኛሉ!

Arsenal, Liverpool Lock Horns in Colossal EFL Semi-Final!
standard.co.uk

ሀሙስ አመሻሽ ላይ ሁለት ትላልቅ የእንግሊዝ እግር ኳስ ቡድኖች በኢኤፍኤል ግማሽ ፍፃሜ ይገናኛሉ! ማን ይሰለፋል እና በዚህ አስደናቂ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያ ምን ሊከሰት ይችላል?

ሁለቱም ቡድኖች በ አፍሪካ ዋንጫ መጀመር ምክንያት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ያጡ ቢሆንም አርሰናል እና ሊቨርፑል በኤፍኤል ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ሀሙስ ምሽት በኤምሬትስ ስታዲየም ያደርጋሉ።

ባለሜዳው ቡድን በሩብ ፍፃሜው ሰንደርላንድን 5-1 በማሸነፍ ወደዚህ ደረጃ ሲደርስ ቀያዮቹ ደግሞ ዕድለኛ ያልሆነውን ሌስተር ሲቲ በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፈዋል።

news.fr-24.com

አርሰናል ከ 1993 ጀምሮ የኢኤፍኤል ዋንጫን አላነሳም ፣ ነገር ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉት መድፈኞቹ ሊቨርፑል ብዙ ተጫዋቾችን በማጣቱ ምክንያት በዚህ አመት ቢያንስ ወደ ፍፃሜው የመግባት እድል እንዳላቸው ጥርጥር የለውም።

ሊቨርፑሎች ቀበሮዎቹን በፍፁም ቅጣት ምት ያሸነፉበትን ግጥሚያ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት 4 ጨዋታዎች ያስመዘገቡት ብቸኛ ድላቸው ነው። አሁን በሰሜን ለንደን ከሚደረገው ፍልሚያ በፊት ኮከብ አጥቂዎቻቸው ሳዲዮ ማኔ እና መሀመድ ሳላህ በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት በግጥሚያው እንደማይገኙ ይታወቃል።

በአርሰናል ቡድን ቶማስ ፓርቲ ፣ ኒኮላስ ፔፔ ፣ መሀመድ ኤልኔኒ እና ፒየር-ኤምሪክ ኦባሚያንግ በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋብርኤል ማርቲኔሊ ከጨዋታ ታግዷል ፣ ሴድ ኮላሲናች ጉዳት ላይ ይገኛል ካሉ ቻምበርስ ደግሞ በኮቪድ-19 ምክንያት አጠራጣሪ ነው።

Albert Sambi Lokoአልበርት ሳምቢ ሎኮንጋ እና አይንስሌይ ማይትላንድ-ኒልስ በአማካይ ስፍራ ይሰለካሉ እና አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ በግብ ክልል ውስጥ በግብ ጠባቂያቸው በርንድ ሌኖ ይተማመናሉ።

football.london

በሊቨርፑል በኩል በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ከሆኑት በተጨማሪ አሊሰን ቤከር ፣ ጆ ማቲፕ እና ሮቤርቶ ፊርሚኖ በኮቪድ-19 ምክንያት በጨዋታው አይካተቱም።

ሆኖም ግን ፣ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እሁድ እለት ከ ሽወርቢ ታውን ጋር ለኤፍኤ ዋንጫ ጨዋታ የቀሩትን ትላልቅ ተጫዋቾች ከማሳረፋቸው በፊት በዚህ ግጥሚያ ጠንካራውን ስብስብ ይዘው ሊገቡ ይችላሉ።

ሊቨርፑል ብዙ ተጫዋቾች በማጣቱ ምክንያት አርሰናል በጥሩ ብቃት ወደ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ የሚያቀና ይመስለናል። መድፈኞቹ በእያንዳንዱ አጋማሽ ግብ አስቆጥረው 2-0 በሆነ ውጤት ያሸንፋሉ ብለን እናስባለን።

የአርሰናል ተጠባቂ አሰላለፍ:
ሌኖ ፤ ቶሚያሱ ፣ ኋይት ፣ ሆልዲንግ ፣ ታቫሬስ ፤ ዣካ ፣ ሎኮንጋ ፤ ሳአ ፣ ኦዲጋርድ ፣ ስሚዝ ሮ ፤ ንኪታህ

የሊቨርፑል ተጠባቂ አሰላለፍ:
ኬልሄር ፤ አሌክሳንደር-አርኖልድ ፣ ጎሜዝ ፣ ቫን ዳይክ ፣ ሮበርትሰን ፤ ጆንስ ፣ ፋቢንሆ ፣ ሄንደርሰን ፤ ጎርደን ፣ ጆታ፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሊን

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EFL Cup