Connect with us
Express news


Football

ስዊንዶን ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል!

Swindon Host Manchester City in Quest for Insane Upset!
swindonadvertiser.co.uk

የሲቲ ኮከቦች በኤፍኤ ካፕ መርሃ ግብር ወደ ስዊንደን ያቀናሉ። የሊግ ቱ ቡድን ተአምር መስራት ይችላል ወይንስ ሲቲ የበላይነቱን ያስቀጥላል?

የማንቸስተር ሲቲ የኤፍኤ ዋንጫ የማሳካት ጉዞ የሊግ ሁለት ቡድን ስዊንዶን ታውን በሶስተኛው ዙር በመፋለን አርብ ምሽት ይጀምራል።

የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን በቀጥታ ወደዚህ ዙር ሲገባ ስዊንዶን ፣ ክሬዌ አሌክሳንድራ እና ዋልሳልን በማሸነፍ ወደዚህ ደረጃ አልፈዋል።

swindontownfc.co.uk

ስዊንዶን ከ1991-92 የውድድር ዘመን በኃላ ከአምስተኛው ዙር ማለፍ አልቻለም ፣ ነገር ግን የሮቢኖች ወደ 4ኛው ዙር የመድረስ ተስፋ በማንቸስተር ኮከቦች የጨለመ ይመስላል።

ሲቲዎች የ2018-19 የፍጻሜ ጨዋታ ዋትፎርድን ሲያሸንፉ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ መሪነት የኤፍኤ ዋንጫን አንድ ጊዜ ብቻ ማሸነፍ ችለዋል። ሆኖም ከ2011-2012 ጀምሮ በማንቸስተር ዩናይትድ 3-2 ከተረታበት ጊዜ አንስቶ ሰማያዊው የማንቸስተር ግማሽ በዚህኛው ዙር ከውድድሩ ተሰናብተው አያውቁም።

በስዊንዶን የቡድን ዜና የክሪስታል ፓላሱ የመሀል ተከላካይ ጄክ ኦብሪየን ዋና አሰልጣኝ ቤን ጋርነርን የተከላካይ መስመር ለማጠናከር በውሰት ቡድኑን ተቀላቅሏል እና የዌልሱ አማካኝ ጆናታን ዊሊያምስ በምርጥ 11 ሊካተት ይችላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሲቲ ፣ ፊል ፎደን እና ኦሌክሳንደር ዚንቼንኮ በ ኮቪድ-19 ምክንያት አጠራጣሪ ናቸው ፣ ስለሆነም ናታን አኬ እንደገና በግራ ተከላካይነት ሊሰለፍ ይችላል ፣ ሲጄ ኢጋን-ሪሊ እና ሉክ ምቤቴ ደግሞ በኋለኛው መስመር መሃል ላይ ለሚገኙ ቦታዎች ይወዳደራሉ።

ዛክ ስቴፈን እና ፈርናንዲንሆ በዚህ ፍልሚያ እንደሚጀምሩ ተስፋ ያደርጋሉ ፣ በአጥቂ ውስጥ ግን ጄምስ ማክቴይ ፣ ኮል ፓልመር እና ኬይኪ ጠቃሚ የጨዋታ ጊዜ ሊያገኙ ይችላሉ።

mancity.com

አንድ አሸናፊ ብቻ አለ ፣ ጥያቄው ሲቲ ስንት ጎል ያስቆጥራል የሚለውን ነው? የጋርዲዮላ ልጆች በመጀመሪያው አጋማሽ 3 ጎሎችን አስቆጥረው 5-0 ያሸንፋሉ ብለን እናምናለን።

የስዊንዶን ታውን ተጠባቂ አሰላለፍ:

ዋርድ ፤ ከስለር ፣ ኦዲማዮ ፣ ሃንት ፣ ኢያንዶ፤ ጊልበርት ፣ ዊሊያምስ ፣ ሪድ ፣ ላይደን ፤ ማኪርዲ ፣ ሲምፕሰን

የማንቸስተር ሲቲ ተጠባቂ አሰላለፍ;

ስቴፈን ፤ ዎከር ፣ ምቤቴ ፣ ኤጋን-ሪሊ ፣ አኬ ፤ ጉንዶጋን ፣ ፈርናንዲንሆ ፣ ማክኤቲ ፤ ካይኪ ፣ ፓልመር ፣ ግሪሊሽ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football