Connect with us
Express news


Football

ሪያል ቫሊንሲያን ባሸነፈበት ግጥሚያ ቤንዜማ እና ቪኒሲየስ ግብ አስቆጥረዋል!

Benzema, Vinícius Bag Braces as Valencia Destroyed by Real!
managingmadrid.com

ሎስ ብላንኮዎቹ ቫሌንሢያን አሸንፈው የላሊጋው መሪነቱት ሲያሰፉ ካሪም ቤንዜማ በሁሉም ውድድሮች 300ኛ ጎሉን ከመረብ አሳርፏል።

የካርሎ አንቸሎቲው ሪያል ማድሪድ ቫሌንሢያን በበርናባው 4-1 በማሸነፍ የላሊጋው መሪነቱን ወደ ስምንት ነጥቦች ከፍ ሲያደርግ ቪኒሲየስ ጁኒየር ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

በመጀመሪያዎቹ 45 ደቂቃዎች ማድሪዶች ግጥሚያውን ተቆጣጥረው የነበሩ ቢሆንም የመክፈቻ ጎል ለማስቆጠር የካሪም ቤንዜማም የፍፁም ቅጣት ምት ግብ መጠበቅ ነበራቸው። አጥቂው በካሲሚሮ ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን እድል ወደ ግብ ለመቀየር አልተቸገረም።

ቪኒሲየስ ከእረፍት መልስ ከካሪም ቤንዜማ ጋር ጥሩ ቅብብል በማድረግ በግብ ጠባቂው ጃስፐር ሲሊሰን መረብ ላይ በማሳረፍ የሪያል መሪነቱን በእጥፍ አሳድጓል። ብዙም ሳይቆይ ብራዚላዊው ተጫዋች ማርኮ አሴንስዮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ከተፋው በኋላ በግንባሩ በመግጨት ሶስተኛውን ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ካሪም ቤንዜማ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩት አራተኛውን ግብ አስገኝቷል።

eurosport.com

ጎንቻሎ ጉዴስ ለአለቃው ሆሴ ቦርዳልስ ቫሌንሲያ አንድ ግብ አስገኝቶ ነበር ነገር ግን ማድሪድ ምቹ በሆነ ሁኔታ አሸንፏል። ውጤቱ መሪዎቹን ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሲቪያን በአምስት ነጥብ በልጠው በ49 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ እንዲቀጥሉ አድርጓል።

ቤንዜማ በ43 ደቂቃ ጎል አስቆጥሯል። ኦማር አልደረቴ በግብ ክልል ውስጥ በካሴሚሮ ላይ በሰራው ጥፋት ባለሜዳው ቡድን ፍፁም ቅጣት ምት እንዲያገኝ ረድቶታል።

ቤንዜማ እድሉን ወደ ግብ በመቀየር በውድድር አመቱ 16ኛው የሊግ ጎሉን አስቆጥሯል ፣ በሪያል ማድሪድም 300ኛ ግቡ ነበር።

በ52ኛው ደቂቃ ላይ ቪኒሲየስ ቤንዜማ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ በማስቆጠር ውጤቱን 2-0 አድርጓል። በመቀጠልም ብራዚላዊው ተጫዋች በግንባሩ በመግጨት ከ9 ደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ አስቆጥሯል።

eurosport.com

በሁለቱም በኩል የጎል እድሎች የነበሩ ሲሆን ቲቦ ኮርቱዋ የዳንኤል ዋስ ሙከራ በጥሩ ሁኔታ አድኖታል ፣ እና የአሴንሲዮ ድንቅ ሙከራ በተከላካዩ ሆሴ ጋይ የወጣ ሲሆን ቫሌንሺያ ግጥሚያው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃ ሲቀረው የፍፁም ቅጣት ምት አኝይተው የማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥረዋል።

ኮርቱዋ የጊዴስን የመጀመሪያ ጥረት ቢያከሽፍም ፖርቹጋላዊው የፊት አጥቂ ግብ ጠባቂው የተፋዉን ኳስ በጭንቅላቱ አስቆጥሯል።

ቤንዜማ ሁለተኛውን ግብ ዘግይቶ በመጨመር ጨዋታው ለእንግዳዎቹ የበለጠ ከባድ እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ከውጤቱ በኋላ በ 28 ነጥብ 9 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football