Connect with us
Express news


Football

ቀያይ ሰይጣኖች በማክቶሚናይ ብቸኛ ግብ አስቶንቪላን አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል!

McTominay on Target to Send Red Devils Past Unlucky Aston Villa!
mirror.co.uk

ስኮት ማክቶሚናይ በመጀመርያዎቹ አስር ደቂቃዎች የማሸነፊያዋን ግብ በማስቆተር ማንቸስተር ዩናይትዶች አስቶንቪላን አሸንፈው በኤፍኤ ካፕ ወደ አራተኛው ዙር ሾልከው እንዲገቡ አድርጓል!

ስኮት ማክቶሚናይ ሰኞ አመሻሽ ላይ በስምንተኛ ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ጎል አስቶንቪላን 1-0 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፉ ያደረገ ሲሆን በኤፍኤ ካፕ አራተኛውን ዙር ጨዋታ ከሚድልስቦሮ ጋር ተገናኝተዋል።

ማክቶሚናይ ወደ ቪላ የግብ ክልል ስድስት ያርድ በእሮጥ ፍሬድ በግራ እግሩ ወደ ውስጥ ቆርጦ ያሻማዉን ኳስ ስኮትላንዳዊ ተጫዋች በጭንቅላቱ በመግጨት በኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ መረብ ላይ አስቆጥሯል።

english.stadiumastro.com

የ8ኛው ደቂቃ ጎል የቪላውን አሰለጣኝ ስቴቨን ጄራርድን ወደ ማንቸስተር በሽንፈት እንዲመለስ ያደረገ ሲሆን ባለሜዳዎቹ ደጋፊዎቸ በተጫዋችነት የሂወት ዘመኑ ለሊቨርፑል ባሳየው ታማኝነት ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር።

የመጨረሻው ውጤት ለጄራርድ እና ከዌስት ሚድላንድስ ለመጡ ሰዎቹ እጅግ ከባድ ነበር። ከእረፍት መልስ ሁለት ጊዜ ኳሷን በዩናይትድ መረብ ላይ ያሳረፉ ቢሆንም ሁለቱም ግቦች ከጭዋታ ውጪ በመሆናቸው ተሽረዋል።

ሁለተኛው ግብ አጥቂው ዳኒ ኢንግስ በግልፅ ከጨዋታ ውጪ የነበረ ቢሆንም የመስመር ዳኛው ኦሊ ዋትኪንስ ኳሱን ወደ ግብ እስኪቀይር ድረስ ባንዲራ አላነሳም።

birminghamworld.uk

ሆኖም የመጀመሪያው የበለጠ አወዛጋቢ ነበር እና ዳኛው በሜዳው አጠገብ ያለውን የቫር ቲሌቭዥን አይተው ውሳኔ እስኪሰጡ ድረስ ጨዋታው ለረጂም ደቂቃ ተቋርጧል። ዳኛው በመጨረሻም አማካዩ ጃኮብ ራምሴ ከጨዋታ ውጪ መሆኑን እና ኢዲሰን ካቫኒን ላይ ጥፋት በመስራቱ ግቡን ሽሮታል።

ቪላ በቅርቡ በኤፍኤ ካፕ ያስመዘገበው ውጤት አስከፊ ነበር። በውድድሩ የመጨረሻ ድላቸው በ2016 ከዋይኮምቤ ዋንደርርስ ጋር ባደረገው የሶስተኛ ዙር የድጋሚ ጨዋታ ነው። በሚቀጥሉት አመታት በማይታመን ሁኔታ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ዋንጫ ውድድር አንድም ጨዋታ ሳያሸንፉ ሰባት የውድድር ዘመን አሳልፈዋል።

በሌላ በኩል የራልፍ ራንግኒክ ቀያይ ሰይጣኖች በቀጣዩ የኤፍኤ ዋንጫ ጨዋታ የካቲት 5 ከቻምፒዮንሺፑ ክለብ ሚድልስቦሮ ጋር ይጫወታሉ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football