Connect with us
Express news


Football

ፒኤስጂ ከግሩፓማ ስታዲየም አንድ ነጥብ ይዞ ተመልሷል!

Underpower PSG Pick Up Point at Groupama Stadium!
dailymail.co.uk

ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን በ ሊግ 1 ከሊዮን ጋር ያደረጉት ፍልሚያ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል። በምሽቱ ፖቸቲኖ ያደረጋቸው የተጨዋቾች ቅያሪ ወሳኝ ነበሩ!

ጀርመናዊው ተከላካይ ቲሎ ከርሀር እሁድ እለት ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ከሊዮን ጋር 1-1 በተለያየበት ግጥሚያ እንግዶቹን ታድጓል ፣ አሰልጣኝ ማርሲዮ ፖቸቲንሆ በሁለተኛው አጋማሽ ያደረጋቸውን የተጨዋቾች ቅያሪ ሎስ ፓሪሴኖች የሊጉን መሪነታቸው ወደ 11 ከፍ እንዲል ረድቷል።

ኬህረር በ69ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባ ሲሆን ከስምንት ደቂቃ በኋላ ፣ ሌላኛው ተቀይሮ የገባው ኤድዋርድ ሚቹት አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ በማስቆጠር ፒኤስጂን በ20 ጨዋታዎች 47 ነጥብ ይዞ አናት ላይ እንዲቀጥል አድርጓል።

cbssports.com

ከውጤቱ በኋላ በ7ኛው ደቂቃ የመችፈቻ ግቡን በሉካስ ፓኬታ አማካኝነት ያስቆጠሩ ሊዮኖች በ25 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ ኒሶች ገና በ20ኛው ደቂቃ ሞርጋን ሽናይደርሊን ቀይ ካርድ ተመልክቶ በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ ቢገደዱም ፣ ከሜዳቸው ውጪ ብሬስቶይስን 3-0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብለዋል።

ፒኤስጂዎች ሊዮኔል ሜሲ እና ኔይማር በኮቪድ-19 እና በጉዳት ምክንያት ከሜዳ በመራቃቸው ክፍተቱን ለመሙላት ተገዷል። ስለዚህም ፖቸቲኖ ማውሮ ኢካርዲን ከ ክሊያን ምብፔ ጋር ለማጣመር ተገዷል።

የፒተር ቦዝ ሊዮኖች በመጀመርያው አጋማሽ ኳሱን ለፒኤስጂ በመስጠት በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት የመረጡ ሲሆን ከአስር ደቂቃዎች ባነሰ ጊዜም ፓኬታ ኪይሎር ብሩኖ ጉማራሬስ ያሻማለትን ኳስ በኬለር ናቫስ መረብ ላይ በማሳረፍ የመክፈቻውን ግብ አስገኝቷል።

sportshub.cbsistatic.com

እንግዶቹ በኪሊያን ምባፔ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ በእጅጉ የሚተማመኑ ቢመስሉም ፈረንሳዊው ኮከብ ተጫዋች በጥሩ ሁኔታ የታጠረው የሊዮን የኋላ መስመር ለማለፍ ሲቸገር ታይቷል።

ሆኖም የፊት አጥቂው ተጫዋች ከእረፍት በፊት የሊዮን መረብ ለመድፈር የሞከረ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ የመታዉን ኳስ የሊዮኑ ግብ ጠባቂ አንቶኒ ሎፔስ አድኖታል።

ፖቸቲኖ አንደር ሄሬራን በ18 አመቱ ታዳጊ ሚቹት ፣ ኮሊን ዳግባን ደግሞ በኬሬር እስኪተካ ድረስ ፒኤስጂ በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ መታገሉን ቀጥሏል።

ሁለቱ ተቀይረው የገቡ ተጫዋቾች ወድያውኑ ፍሪያማ መሆን ችለዋል እናም ፒኤስጂ ደካማ እንቅስቃሴ ባሳየበት ግጥሚያ ላይ ተቀያሪዎቹ ለቡድናቸው አንድ ነጥብ ማስገኘት ችለዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football