Connect with us
Express news


EFL Cup

በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሜሲሳይድ ተቀናቃኞች ሊቨርፑል እና አርሰናል ይገናኛሉ!

Massive Merseyside Semi-Final as Reds Take on Arsenal!
liverpooloffside.sbnation.com

ሁለቱ ትልልቅ የእንግሊዝ እግር ኳስ ቡድኖች ሐሙስ ምሽት በሊቨርፑል ሲገናኙ ምን ሊከሰት ይችላል?

በኮቪድ-19 ሀሰተኛ የምርመራ ውጤት ዙርያ በተነሳ ውዝግብ ውስጥ የሚገኘው ሊቨርፑል ሐሙስ ምሽት በኢኤፍኤል ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በአንፊልድ አርሰናልን ያስተናግዳል።

ሊቨርፑል በቅርቡ ባቀረበው ሀሰተኛ የ ኮቪድ-19 የምርመራ ውጤት እንደገና ምርመራ ሊደረግበት ይችላል። እንዲህ ዓይነቱ ከፍተኛ ቁጥር ፈጽሞ የማይቻል ነው ተብሎ ይታሰባል! ሆኖም የታዳጊዎች እና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች የያዘው ስብስባቸው በሳምንቱ መጨረሻ በኤፍኤ ካፕ ሽሬውስበሪ ታውንን 4-1 በሆነ አሳማኝ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአርቴታ ቡድን አስደናቂ ጨዋታዎችን አድርጎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መድረስ ችሏል። በዌስትብሮሚች አልቢዮን ፣ ዊምብልደን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ሰንደርላንድ ላይ ባደረጓቸው አራት ድሎች በአጠቃላይ 16 ጎሎችን አስቆጥረዋል። አሁን በሰሜን ለንደን አርሰናል ከ1992/93 የውድድር ዘመን በኋላ የመጀመሪያውን የኢኤፍኤል ዋንጫ ማንሳት ይችላል የሚል ስሜት አለ።

expressandstar.com

በቡድን ዜና ፣ ሊቨርፑል አሊሰን ቤከርን ከ ኮቪድ-19 ያገገመ ሲሆን ፣ ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ አሁን በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የተረጋገጠ ብቸኛው በኮቪድ – 19 የተጠቃ ተጫዋች ነው።

ሳዲዮ ማኔ ፣ መሀመድ ሳላህ እና ናቢ ኬይታ በ አፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ስለማይገኙ ጆርዳን ሄንደርሰን ፣ ዲዮጎ ጆታ እና ካይዴ ጎርደን በዚህ ሳምንት በምርጥ 11 ሲካተቱ ማየት የሚያስደንቅ አይሆንም።

dailytelegraph.co.uk

አርሰናልን በተመለከተ ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ ፣ ሞሃመድ ኤልኔኒ ፣ ቶማስ ፓርቴይ እና ኒኮላስ ፔፔ በጉዳት አልያም በ አፍሪካ ዋንጫ ምክንያት በጨዋታው የማይገኙ ሲሆን ጋብርኤል ማጋሌሄስ በወሳኝ ሰአት ከቅጣት ተመልሷል።

football.london

ግራኒት ዣካ እና ፎላሪን ባሎጋ በኮቪድ-19 ምክንያት ግጥሚያው ያመልጣቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ኤሚሌ ስሚዝ ሮዌ እና ታኬሂሮ ቶሚያሱ በጉዳት ምክንያት አጠራጣሪ ናቸው።

ኤዲ ንከታህ በኤፍኤል ካፕ ግብ በማስቆጠር ላይ ይገኛል ነገር ግን የ22 አመቱ ወጣት በኤፍኤ ካፕ ያሳየው አሳዛኝ እንቅስቃሴ አርቴታ አሌክሳንደር ላካዜትን የፊት መስመር የመምራት እድልን ሊሰጠው ይችላል።

በሁለቱ ቡድኖች ብዙ ተጫዋቾች ባጡበት ሰአት ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብለን እንጠብቃለን። የክሎፕ ተጫዋቾች የመክፈቻውን ግብ አስቆጥረው ሁለቱም ግቦች በሁለተኛው አጋማሽ ይቆጠራሉ ብለን እናስባለን።

Liveየሊቨርፑል ተጠባቂ አሰላለፍ:
አሊሰን ፤ ብራድሌይ ፣ ማቲፕ ፣ ቫን ዳይክ ፣ ቲሚካስ ፤ ሄንደርሰን ፣ ፋቢንሆ ፣ ጆንስ ፤ ጎርደን ፣ ጆታ ፣ ሚናሚኖ

የአርሰናል ተጠባቂ አሰላለፍ:
ራምስዴል ፤ ቶሚያሱ ፣ ኋይት ፣ ጋብርኤል ፣ ቲየርኒ ፤ ሎኮንጋ ፣ ፓቲኖ ፤ ሳካ ፣ ኦዴጋርድ ፣ ማርቲኔሊ ፤ ላካዜት

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EFL Cup